ኢትዮጵያ ለሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ የ15 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንደምትሰጥ ገለጸች::
በአዲስ አበባ በተካሄደው የሱዳን ሰብዓዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ 217 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ተዋጥቷል::
በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሰራዊት መካከል እየተካሄደ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት እንደቀጠለ ይገኛል።
በዚህ ጦርነት ምክንያት 30 ሚሊዮን ሱዳናዊያን ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚስፈልጋቸው ተመድ አስታውቋል።
እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሱዳናዊያን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ማሰባሰብን ዓላማው ያደረገ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒ ጉቴሬዝ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀማት፣ የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ፣ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬት ሚንስትር ዴኤታ ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን እና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።
የጉባኤው አዘጋጅ ከሆኑት መካከል አንዷ የሆነችው የተባበሩት አረብ ኢምሬት 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጋለች።
Via አል ዐይን ኒውስ