የትግራይ ክልል ነዋሪዎች በፍርሀት ክልሉን ለቀው ለመሸሽ እያሰቡ መሆኑን ኤኤፍፒ ዘግቧል‼️
በአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደርና በህወሀት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መካከል የተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ ወደ ውጥረት መሻገሩን የጠቀሰው ዘገባው አንደኛው አንጃ በመቀሌ የሚገኘውን ማዘጋጃ ቤት መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡
አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር ለዜና አውታሩ ሲናገር ‹‹አሁን ህዝቡ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ካለፈው የከፋ ሁኔታ ሊያጋጥም ይችላል በሚል ስጋት ላይ ነው›› ብሏል፡፡ ሌላ ነዋሪ ደግሞ ህዝቡ ክልሉን ጥሎ ለመሸሽ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ገልፃለች፡፡ ምህረት የተባለችው ይህች የ27 አመት ወጣት ስትናገር ‹‹ባለፈው ጦርነት ጊዜ በመቀሌ ውስጥ ታሽገን ነበር፡፡ አሁን ያ እንዲደገም አንፈልግም፡፡›› ብላለች፡፡
ጨምራም ‹‹አሁን ክልሉን ለቀን ለመውጣት ጥረት እያደረግን ነው፡፡ ነገር ግን የአውሮፕላን ትኬት ለመቁረጥ ስንፈልግ ሰሞኑን ያሉት በረራዎች የሞሉ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡ ስለዚህም ክልሉን ለመልቀቅ ሌሎች አማራጮችን እየፈለግን ነው›› በማለት አስረድታ ነዋሪው በፍርሀት ውስጥ እንደሚገኝ ገልፃለች፡፡
እንደኤኤፍፒ ዘገባ የደብረፅዮን አንጃ የመቀሌ ከተማን ማዘጋጃ ቤት ትላንት የተቆጣጠረ ሲሆን የራሱን ከንቲባም ሾሟል፡፡ እንዲሁም በመቀሌ የሚገኘውን የኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ በቁጥጥሩ ስር አስገብቷል፡፡ የዶክተር ደብረፅዮን ቃል አቀባይ ለዜና አውታሩ ሲናገሩ ‹‹ቀደም ሲል ተመርጠው የነበሩት ከንቲባ በአቶ ጌታቸው ረዳ ተባረው ነበር፡፡ ያ ደግሞ ህጋዊ አልነበረም፡፡ ስለዚህም አሁን እኚያን ከንቲባ መልሰን ሾመናቸዋል›› ብለዋል፡፡
Via- አዩ ዘ ሀበሻ