🫧ስለ 5ጂ ሰምተው ተደንቀው ይሆናል፤ የ6ጂ መንገድ መጀመሩን ቢያውቁስ?
🧵የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሪካል መሐንዲሶች እስከ 100 ጊጋኸርዝ ባለው የራዲዮን ፍሪኩዌንሲ መስራት የምትችል ገመድ አልባ ትራንሲቨር ሰርተዋል፡፡
🧵ይህም በአሁኑ ሰዓት በግንባታ ላይ ካለው የአምስተኛው ትውልድ ገመድ አልባ ግንኙነት (#5ጂ) መስራት ከሚችለው አራት እጥፍ የላቀ ነው፡፡
🧵በፈጣሪዎቿ “#end-to-end transmitter-receiver” የሚል ስያሜ የተሰጣት ይህች ባለ 4.4 ካሬ ሚ.ሜ ቺፕ ለተላበሰችው የተለየ የዲጂታል-አናሎግ አወቃቀር ምስጋና ይግባውና ዲጂታል ሲግናሎችን ፈጣንና ኃይል ቆጣቢ በሆነ መልኩ ማንቀሳቀስ ትችላለች፡፡
🧵በዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሪካል ምህንድስና እና ኮምፒውተር ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ፓያም ሄይዳሪ አዲሱ ፈጠራቸው የሚያቀርበው የፍጥነት እና ዳታ መጠን ከአዳዳሶቹ የገመድ አልባ ግንኙነት ደረጃዎች እንኳን ሲነፃፀር በሁለት #orders of magnitude የላቀ መሆኑን በመጥቀስ መሳሪያውን 5ጂን የተሸገረ ብለውታል፡፡
🧵ይህ እውነት አለው፡፡ #5ጂ መስራት የሚችለው ከ28 እስከ 38 ጊጋ ኸርዝ ባለው ገደብ ውስጥ ነው፡፡ በሌላ መልኩ #6ጂ ከ100 ጊጋ ኸርዝ በላይ እንደሚሰራ ይጠበቃል፡፡
🧵ይህች አነስተኛ ቺፕ ዳታን በከፍተኛ ፍጥነት ማዘዋወር መቻሏ የነገሮች ከበይነ-መረብ ጋራ ያላቸው ትስስር (#Internet Of Things) እየላቀ በመጣበት በዚህ ወቅት እጅጉን አስፈላጊ ያደርጋታል፡፡
🧵ከዚህም ባሻገር መረጃን በማዘዋወር ረገድ ያላት ፍጥነት ከገመድ ጋር ተወዳዳሪ ስለሆነ እንደ ዳታ ሴንተር ባሉ ስፍራዎች ላይ የሚታየውን ከፍተኛ የገመድ ዝርጋታ እና እርሱን ተከትሎት የሚመጣውን ከፍተኛ ወጪንም እንደምትቀንስ ይጠበቃል፡፡