ኢንተርኔት በምንጠቀምበት ጊዜ ማንነታችንን እንዴት መደበቅ እንችላለን (የመጨረሻ ክፍል)ታድያ እነዚህ መረጃዎች እንዳይያዙብን ከፈለግን የሚቀጥሉትን ሶስት መንገዶች ተጠቅመን ማንነታችችንን እና መረጃዎቻችንን መደበቅ እንችላለን
ፕሮክሲ ሰርቨር፡ ፕሮክሲ ሰርቨር አይፒ አድሬሳችን በዌብ ሰርቨሮች እንዳይታይ የሚያደርግልን ሰርቪስ ነው። በተለይም ኦንላይን ዌብ ሰርቨሮችን በመጠቀም የምንፈልገውን ዌብሳይት ቀጥታ ሰርች ማድረግያው ላይ በመጻፍ አይፒ አድራሻችንን መደበቅ እንችላለን። የዚህ አገልሎት መጥፎ ጎን የኢንተርኔት ፍጥረቱን ዝግ ማድረጉ ነው። ከኦንላይን ዌብ ፕሮክሲዎች መካከል
https://www.proxysite.com/ ይጠቀሳል
ፌክ ኢሜል አካውንት፡ ዌብሳይቶችን ስንጠቀም ኢሜይላችንን ተጠቅመን ሎግኢን እንድናደርግ ይጠይቃሉ ለዚህ አግልጎሎት ትክክለኛ ኢሜይላችንን ከመጠቀም አንድ ፌክ እና ብዙ መረጃዎቻችንን ያልያዘ ኢሜል አካውንት ፈጥረን በሱ መጠቀም ከመረጃ መንታፊዎች ያድነናል።
የብሮውሰር ሂስትርያችንን እና ኩኪያችንን ማጥፋት፡ የምንጠቀምበትን ብሮውሰር አይነት በመለየት የብሮውሰር ሂስትሪያችንን ማጥፋት። ሌላው ደግም ብሮውሰራችን ላይ third party cookieን ማጥፋት አሪፍ መፍትሄ ነው።
ምሳሌ፡ ክሮም ላይ third party cookieን ለማጥፋት እነዚህን መመርያዎች መከተል እንችላለን
1) ከላይ በቀኝ በኩል ሶስት ነጥብ መጫን
2) settingን መጫን ከዛ privacy and security መጫን
3) third party cookie የሚለውን በመጫን
4) Block third-party cookies የሚለውን በመጫን ዌኤባስይቶች ኩኪ እንዳዪዙ ማድረግ እንችላለን።
#techhelp
#online_privacy
#Cantech