የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተደራሽነቱን ከሀገር ውጭ ማስፋት እንዳለበት ተገለፀ፡፡
የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) የባንኩን የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ገምግሟል፡፡
**************************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ገምግመዋል፡፡
በግምገማው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ በተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ የተመዘገበው ውጤት አበረታች መሆኑ እና በዚህ እረገድ የገበያ ድርሻውን ማሳደግ መቻሉ ታይቷል፡፡
ዲጂታል የባንክ አገልግሎትን ከማስፋት አንፃር በባንኩ የተመዘገበው ውጤት እንዲሁ ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የባንኩ አጠቃላይ የተበላሹ ብድሮች ክምችት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ሌላው በባንኩ የተመዘገበው አበረታች ውጤት መሆኑ ተነስቷል።
በሲቢኢ ኑር አገልግሎት የተመዘገበው አፈፃፀም በአብዛኛው መለኪያዎች በጣም ጥሩ የሚባል መሆኑ ተገምግሟል፡፡
በብድር አሰጣጥ ረገድ ከፍተኛ መሻሻል የታየ ቢሆንም፣ ከባንኩ ብድር ተደራሽነት አንፃር እና ከብድር አሰጣት ሂደት ጋር ተያይዞ ክፍተቶች እንዳሉ እና በዚህ እረገድ የደንበኞች እርካታ የቀነሰ መሆኑ ተነስቷል፡፡
ባንኩ ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ በማዘጋጀት ላይ መሆኑ ሊመሰገን የሚገባው መሆኑም በውይይቱ ተነስቷል።
የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ ረገድ ያስመዘገበውን አበረታች ውጤት ማስቀጠል እና የገበያ ድርሻውን ይበልጥ ማሳደግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ብሩክ የባንኩን የብድር አሰጣጥ ሂደት ዲጂታላይዝ በማድረግ እና ተደራሽነቱን ይበልጥ በማሳደግ የደንበኞችን እርካታ ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ባንኩ አገልግሎቱን በዲጂታል አማራጮች ማስፋቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ያሳሰቡት ዶክተር ብሩክ፣ ነገር ግን የህብረተሰቡን የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን የመጠቀም ችሎታም ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡
ዶክተር ብሩክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀገር ውጭ ያለውን ተደራሽነት ከጅቡቲ እና ደቡብ ሱዳን ባሻገር በሌሎች አካባቢዎችም ለማስፋት መሥራት እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡
ዶክተር ብሩክ የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር በሚገቡበት ወቅት የሚያጋጥመውን ውድድር ለማሽነፍ እና የገበያ ድርሻውን አስጠብቆ ለማስቀጠል የሚያስችል ስትራቴጂ ከወዲሁ መንደፍ እንደሚያስፈልግም ለዚህም ከተቋማቸው ሙሉ ድጋፍ እንደሚደረግለት ገልፀዋል።