የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ 1.54 ትሪሊዮን ብር ደረሰ።
**************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ዛሬ ከኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) የሥራ ኃላፊዎች ጋር በነበረው የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ እንደተናገሩት፣ የባንኩ አጠቃላይ የሥራ አፈፃፀም መልካም መሆኑን ጠቅሰው በበጀት ዓመቱ እስከ የካቲት 16 ቀን 2017 ድረስ የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ ከ350 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን እና የባንኩ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ 1.54 ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱን ጠቁመዋል።
አቶ አቤ አጠቃላይ በባንኩ ከተፈጸሙ የገንዘብ ግብይቶች 84.5 በመቶ የሚሆነው በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የተፈጸሙ መሆናቸውን ጠቅሰው ይህም አበረታች እንደሆነና የአገልግሎት ጥራቱንም ይበልጥ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የብድር አገልግሎት በሚቀጥሉት 5 ዓመታት የባንኩ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አቤ፣ በዘንደሮው የበጀት ዓመት ጠቅላላ የብድር መጠን ወደ 1.35 ትሪሊየን ብር ማደጉን እና በቅርቡም አዳዲስ የብድር ዓይነቶችን በተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ለባንኩ ደንበኞች በማስተዋወቅ የብድር ተደራሽነቱን ለማሳደግ እንደሚሠራ አመላክተዋል።