የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ1446ኛ ዓ.ሒ የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ በመቐለ ከተማ ለሚኖሩ አቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሄደ።
• ድጋፍ የተደረገላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎት ለባንኩ ምስጋና አቅርበዋል።
**************************
በመርሃ ግብሩ ላይ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቐለ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ልሳነ ወርቅ ባንኩ "አብሮነት ለበጎነት፣ በረመዷን" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ የማዕድ ማጋራት እና ሌሎች መርሀ ግብሮችን እያካሄደ መሆኑን በመግለፅ ይህም የሕብረተሰቡ አለኝታነቱን ለማሳየት ነው ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ አደም ዓብድልቃድር ባንኩ በክልሉ የሚፈፅመው መልካም ተግባር ከሚሰጠው አገልግሎት ባሻገር ህዝባዊነቱን ያስመሰከረበት መሆኑን ገልፀው ፣ ይህም የሚመሰገን እና ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር ነው ብለዋል፡፡
የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ሐጅ መሀመድ ካሕሳይ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለህዝበ ሙስሊሙ አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረጉ የሚያስመሰግነው መሆኑን በመግለፅ፣ በክልሉ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
በማዕድ ማጋራቱ ድጋፍ የተደረገላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በበኩላቸው ባንኩ ላደረገው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል።