የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሃን ዲስትሪክት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አከናወነ።
***************************************************************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ “በፋሲካ ፍቅርን እንግለጽ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ አካባቢዎች ካካሄደው የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር ጋር በተያያዘ ደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ለ700 ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ማዕድ አጋርቷል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረብርሃን ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ጨበር እንደገለጹት በባንኩ በተመደበ በጀት እና የባንኩ እና የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሰራተኞች ባደረጉት የ500 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ በደብረ ብርሃን፣ በመሀል ሜዳ፣በሸዋ ሮቢት፣በለሚ፣በዓለም ከተማ፣በሞላሌ እና በአረርቲ ማዕድ ማጋራቱ ተካሂዷል።
አቶ ሮቤል በቀጣይም ባንኩ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚወጣ አስታውቀዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ የተከበሩ ወርቃለማሁ ኮስትሬ እና የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ የተከበሩ ተክለየስ በለጠ ባንኩ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን በርካታ የልማት ራዎችን በማከናወን ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ ለተደረገው የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መጋቢ ሀዲስ ነቃጥበብ አባቡ በበኩላቸው ሁሉም በዓሉን ያለውን በማካፈል እንዲያከብር አሳስበው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ ማጋራቱ የሚበረታታና የሚያስመሰግን በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡