በቃል ሲነገራት የፍቅር አጥናፉ፥
ደሞ እንደሚያስደስት በጋራ ሲከንፉ፤
አታምንም ልጅቱ...
ስለምትሰማ ነው ውሸት በየቤቱ፤
...
...
ማፍቀር መታደል ነው
መፈቀርም መክበር፤
የበደነ ገላ ሊሞት እንዲሳፈር፤
የቀናለት መስመር
ብለናትም ነበር .......
ግና የት አባቱን የፍቅር መጃጃል፤
በጠርጣሪ ልብ ውስጥ ፍርሃት ይዋጃል።
..
..
አጥብቃ ጠይቃ እምነትን ካልፃፈች፤
በፍርሀቷ ግርዶሽ ፍቅር ለምኔ ካለች፤
ያው መንገድ ጠቁሟት....
የጥላቻን ድልድይ
ደም የተፃፈበት የሚታይ እንደ እኩይ፤
ግሳት ብቻ ያለበት ጥጋብ ብቻ ቤቱ፤
በቀይ የተደራ የደም ልብስ ሌማቱ፤
የከበበውን ደጅ.....
እንኳንስ ለሰው ልጅ ለእንስሳም እማይበጅ፤
መሆኑን ስታየው .....
ፍቅር ወዴት አለህ ምትል ይመስለኛል፤
እሱ ካልቀረበ ሰላም የት ይገኛል።
#ሚኪ
ደሞ እንደሚያስደስት በጋራ ሲከንፉ፤
አታምንም ልጅቱ...
ስለምትሰማ ነው ውሸት በየቤቱ፤
...
...
ማፍቀር መታደል ነው
መፈቀርም መክበር፤
የበደነ ገላ ሊሞት እንዲሳፈር፤
የቀናለት መስመር
ብለናትም ነበር .......
ግና የት አባቱን የፍቅር መጃጃል፤
በጠርጣሪ ልብ ውስጥ ፍርሃት ይዋጃል።
..
..
አጥብቃ ጠይቃ እምነትን ካልፃፈች፤
በፍርሀቷ ግርዶሽ ፍቅር ለምኔ ካለች፤
ያው መንገድ ጠቁሟት....
የጥላቻን ድልድይ
ደም የተፃፈበት የሚታይ እንደ እኩይ፤
ግሳት ብቻ ያለበት ጥጋብ ብቻ ቤቱ፤
በቀይ የተደራ የደም ልብስ ሌማቱ፤
የከበበውን ደጅ.....
እንኳንስ ለሰው ልጅ ለእንስሳም እማይበጅ፤
መሆኑን ስታየው .....
ፍቅር ወዴት አለህ ምትል ይመስለኛል፤
እሱ ካልቀረበ ሰላም የት ይገኛል።
#ሚኪ