የኢማሙ ሶላት ቢበላሽ የተከታዮቹ ይጠፋልን?
~
ኢማም የሆነ ሰው ሶላቱን የሚያበላሽ ነገር ቢፈፅም የተከታዮች ሶላት አይብበላሽም። ለምሳሌ ኢማሙ ረስቶት ያለ ውዱእ ቢያሰግድ ተከትለውት የሰገዱ ሰዎች ሶላት አይበላሽም። ዑመር ብኑል ኸጧብ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ረስተው በጀናባ ላይ ሆነው አሰግደዋል። የራሳቸውን ሶላት የመለሱ ሲሆን ነገር ግን ሌሎች ደግመው እንዲሰግዱ አላዛዙም። [ ማሊክ፡ 1/49] [በይሀቂይ: 1/170]
በተመሳሳይ ተከታዩ ውዱእ ወይም ሶላት ያጠፋሉ ብሎ የሚያስባቸው ጉዳዮች ኢማሙ ዘንድ የሚያጠፉ ካልሆኑ ተከትሎ መስገድ ይቻላል። ለምሳሌ ኢማሙ ብልትን መንካት ውዱእ አያጠፋም ብሎ ያምናል። ተከታዩ ደግሞ ያጠፋል ብሎ ነው የሚያምነው። በእንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ኢማሙን መከተል ምንም ችግር የለውም። እንዲያውም መከተል ነው ያለብን። [አልፈታዋ፡ 23/375 - 378]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor