ጥሪ ወደ ተውሂድና ሱና(الدعوة إلى التوحيد والسنة)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ ቻናል የተለያዩ የሱና ፅሁፎች ና ኣንዳንድ የድምፅ ፋይሎች የምተላለፉበት ቻናል ነው፡፡

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ጥቂት የታላቁ ዓሊም ❨ሊቅ❩ ሸይኸ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁሏህ) ህይወት ታሪክ በራሳቸው አንደበት ከመጅሙዑል ፈታዋ የተወሰደ።

ስሜ ዐብዱል'ዐዚዝ ኢብን ዐብዱሏህ ኢብን ዐብዱር-'ረሕማን ኢብን ሙሐመድ ኢብን ዐብዱሏህ ኢብን ባዝ ይባላል።የተወለድኩት እንደ ሒጅራ አቆጣጠር በዙል ሒጃ፣1330 ዓ.ሂ በሪያድ ከተማ ነው። ዒልም በጀመርኩበት ጊዜ ማየት እችል ነበር። ከ 16 ዓመት በኃላ ማለትም 1346 ዓ.ሂ ዓይኔን ታመምኩኝ። ዐይኖቼ ደከሙ። ከ 4 አመት በኃላ ማለትም በ1350 ዓ.ሂ አላህ የተመሰገነ ይሁንና ሁለቱም ዓይኖቼ ጠፉ። የውስጥ መመልከቻዬን በጥልቀት መመልከት እንድችል ሃያሉ ጌታዬን እጠይቃለሁ። በዱንያም በአኼራም መጨረሻዬን እንድያሳምርልኝ እጠይቃለሁ ።
ዒልም የጀመርኩት በልጅነቴ ነበር። ቁርዓንንም የሀፈዝኩት በወጣትነት ጊዜ ነበር። ከዚያም ኢስላማዊ እውቀቶችን፣አረብኛ ቋንቋን ሪያድ ከሚገኙ ዑለማዎች ተማርኩኝ። እኔ እውቀቶችን የተማርኩባቸው ዑለማዎች ስም ዝርዝራቸው እንደሚከተለው ነው:

1⃣➺ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ዐብዱል'ለጢፍ ኢብን ዐብዱር-ረሕማን ኢብን ሐሰን ኢብን አሽ-'ሸይኸ ሙሐመድ ኢብን ዐብዱል-'ወሓብ ❨ረሒመሁሏህ)

2⃣➺ሸይኽ ሷሊህ ኢብን ዐብዱል-'ዐዚዝ ኢብን ዐብዱር-'ረሕማን ኢብን ሐሰን... (ረሒመሁሏህ)

3⃣➺ሸይኽ ሰዓድ ኢብን ሐማድ ኢብ ዐቲቅ (ረሒመሁሏህ)

4⃣➺ ሸይኽ ሐማድ ኢብን ፋሪስ (ረሒመሁሏህ)

5⃣➺ሸይኽ ሰዓድ ወቃስ አል-ቡኻሪ (ረሒመሁሏህ) እኝህ ሸይኽ ከመካ ዓሊም አንዱ ሲሆኑ ተጅዊድን ተምሬባቸዋለሁ።

6⃣➺ በተራ ቁጥር አምስት የተቀመጡት ዝነኛ ሸይኻቸው ሙሐመድ ኢብን ኢብራሂም ኢብን ዐብዱል-'ለጢፍ (ረሒመሁሏህ) በኝህ ሸይኽ ለ10 ዓመት ያክል ተምሬባቸዋለሁ። የተማርኩባቸው ሁሉንም የዒልም ዓይነቶችን ነው፣ ከ 1347 እስከ 1357 በሳቸው ተምሬያለሁ ይላሉ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁሏህ)።ለፈትዋም እንድመረጥ ያደረገኝ እኝሁ ሸይኽ ናቸው። ሁላቸውንም አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይከፈላቸው!!!!

በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይም ተሹሜያለሁ

⓵- የኽርጅ አከባቢ ከ1357-1371 ዓ.ሂ በጀማደ ሳኒ 1357ዓ.ሂ ተሹሜ ለ14 ዓመት ያክል በሸሪዓዊ ዳኝነት ቆይቻለሁ።

➁- ሪያድ የሚገኘው በሐዲስ ፋካሊቲ (faculty) ተቋም፤ተውሒድን፣ፊቅህን.. faculty of shari'ah በ1373 ዓ.ሂ ከተመሰረተ በኃላ ለ 9 አመት አስተምርያለሁ።በዚህ ተቋም እስከ 1380 ዓ.ሂ ቆይቻለሁ።

➂-በ1381ዓ.ሂ በመዲና ዩኒቨርሲቲ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ተሹሜ እስከ 1390 ዓ.ሂ ቆይቻለሁ።

➃-በ1390 የቀድሞው የመዲና ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ኢብራሂም (ረሒመሁሏህ) ከሞቱ በኃላ በሳቸው ቦታ ከ1390 እስከ 1395 ዓ.ሂ ቆይቻለሁ።

➄- በቀን 20/1/1414 ዓ.ሂ የሳዑዲ መንግስት  አጠቃላይ ሙፍቲ አድርጎ ሾመኝ። እስካሁን በዚሁ እርከን ላይ እገኛለሁ። አላህ እንዲረዳኝና ትክክለኛውን ብይን እንዲለግሰኝ እጠይቃለሁ።

በተጨማሪም በዚህ ጊዜ የተለያዩ ኢስላማዊ ካውንስሎች ላይ በአባልነት ቆይቻለፀ፣ ለምሳሌ ያክል፦

◆ የሳዑዲ አረቢያ የዑለማዎች ፕሬዝዳንት council።

◆ የሳዑዲ አረቢያ የዳዕዋ council

◆ የመዲና ዩኒቨርሲቲ ኢስላማዊ council

◆የአለም አቀፍ መስጂዶች ፕሬዘዳንት council...

የፃፍኳቸው መጽሐፍቶችን በተመለከተ:

1) አል-ፈዋኢድ አል-ጀ
ሊያህ ፊ አል-መባሂስ አል-ፈርዲያ

2) አት-ተህቂቅ ወል-ኢዳህ ሊ-ከሲር ሚን-መሳኢል አል-ሐጅ ወል-ዑምራህ ወዝ-ዚያራህ

3)አት-ተህዚር ሚነል ቢድዓ (ይህ ኪታብ በውስጡ ያቀፈው መወለድን በተመለከተ፣የኢስራዕ ሌሊት፣ የሻዕባን ግማሽ፣...በውስጡ አቅፎ ይዟል።

4) አል-ዐቂዳህ አስ-ሶሂሃ ወማ የዱ'ዱሃ

5)ውጁብ አል-አመል ቢሱነቲ ረሡል።

6)ዳዕዋህ ኢለላህ ወ'አኽላቅ አድ'ዱዓ

7)ዉጁብ ተህኪም ሸሪ'አላህ

8)ሁክሙ አስ-ሱፉር ወ' አል-ሒጃብ ወን-ኒካህ...

9) ነቅድ አል-ቀውሚያህ አል-አረቢያ

10) አል-ጀዋብ አል ሙፊድ ፊ ሁክሚ አት-ተስዊር

11) ታሪኽ ሸይኽ ሙሐመድ ዐብዱል'ወሓብ..

12) ሶላት..

13) ሁክም አል-ኢስላም ፊ-መን ተዓና ፊል-ቁርዓን አው ፊ'ረሡል

15) ሃሺያህ አል-ሙፊዳህ ዐላ ፈትሁል ባሪ

16) ኢቃም አል-በራሂን ዐላ ሁክም መን ኢስቲጋሳ ቢገይሪላህ...

17) አል-ጂሃድ ፊ ሰቢሊላህ

18) አድ-ዱሩስ አል-ሙሂማህ ሊ ዓመቲል ዑማህ

19) ፈታዋ ተተዐለቅ ቢ አሕካም አል-ሐጅ ወል-ዑምራህ

20) ውጁብ ሉዙሙ ሱናህ...

[መጅሙዑል ፈታዋ፣ጥራዝ:1 ገጽ:9-12]

✍ ትርጉም፦ሰሚር ጀማል


Forward from: أبو فوزان عبدالسلام
ኑ" በኮምቦልቻ የሚገኘውን የሰለፍዮች መስጂደ ሰላምን ተባብረን እንስራ።
▶ ይህ ግሩፕ የተከፈተበት አላማ በኮምበልቻ ሰለፍዮች የተጀመረዉን የመስጂደ ሰላም ግንባታን ለማፋጠን የናተን የወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ትብብር በመሻት ነው።
وقال النبي صلى الله عليه وسلم : ( مَنْ بَنَى مَسْجِدًا بَنَى اللَّهُ لَهُ   مِثْلَهُ فِي الْجَنَّةِ ) رواه البخاري
ومسلم

🔵 ማስታወሻ፦ ሊንኩን ሸር እና ሰዎችን አድ በማድረግ ይተባበሩን

➡️ ወደ ግሩፑ ለመቀላቀል ከታች ያሉትን ሊንኮች በመጫን ይቀላቀሉን
      👉 👉👉የቴሌግራም ግሩፕ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

https://t.me/kombolcha_selam_mesjd
    👉👉👉      የዋትሳፕ ግሩፕ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

https://chat.whatsapp.com/D2UB2KRGRXn1fGo0RTh6qS

‼️ጥንቃቄ !!! ወደባንክ ገቢ ስታዴርጉ  የ3ቱንም ሰዉ ስም ፅፋችሁ መሆን አለበት። በሞባይል ትራንስፈር ለምታደርጉ ደግሞ አካውንት ቁጥሩን ስታስገቡለት አሁንም የ3ቱንም ሰው ስም መምጣቱን እርግጠኛ መሆን አለባችሁ።
➡️አካዎንቱ እና ስሙ ፕሮፋይሉ ላይ ወይም ግሩፑ ስም ላይ አለላችሁ።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ልብስ መገተት ሀራም ነው
ክፍል ሁለት


ልብስ መጎተት ሀራም ነው
ክፍል አንድ




የመጅሊስ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆኖ በተመረጠበት፣ ሱናን የሚሞግቱ ሰዎች ሳይቀር ደስታቸውን በገለፁበት ምርጫ የተመረጠው ከላይ እንደሚትመለከቱት በሶለዋት ስም የሚደረጋውን ጭፈራ የሚመራ #አብዱልከሪም በድረዲን የሚባል ግለሰብ ነው። ትላንት በኢኽዋኖች እርስ በርስ ጥቆማ የተመረጠውን ኮሚቴ የተሰኛውን ምርጫ ያልተቀበሉ ሰለፊዮች ዛሬ ላይ #የአጥፊው የሱፊያ አመለካከት አራማጅ ፣ #የገሪባ ሀድራን የሚመራ፣ #ቢድዐ የሆነውን መውሊድን የሚያከብር፣ #ድቤ የሚደበድብ ሰው የተመረጠበት ምርጫ እንዴት ሆነው ነው እንደመልካም የሚቆጥሩት?! ይህ ኽያና(ማጭበርበር)፣ ከአቋም መውረድ ፣ የሰለፊያን መንገድ ማቅለጥ ካልሆነ የትኛው ጥፋት ነው በነዚህ የሚገለፀው?! ድሪብርብ የሆነ ጥፋቶች ተከስተው ይቅርና ሰለፎች አንድ እንኳ መሰረታዊ የሆነ ዲንን የሚሸረሽር ጥፋትን ከማዎቅ ጋር ባጠፋ ሰው ላይ ጥንካሬያቸው እንዴት እንደነበር ረሳነው እንዴ?!
ከዚያ ከሰፊው በተለያዩ ኪታብ ጥራዞች ተጽፎ ከሚገኛው የብድዐ ሰዎችን አስመልክቶ ከሰለፎች ከመነጨው ንግግር ከባህር በመርፌ እንደመጭለፍ ቢሆንም የሶስት የደጋግ ቀደምት ንግግሮችን ላስፍር: -
¢አብዱሏህ ብን መስዑድ(ረድየሏህ ዐንሁ) " የብድዐ ሰዎችን አትቀማመጥ! እነሱን መቀማመጥ ለቀልብ በሽታ ነው"
¢ፉዷይል ኢብኑ ዒያድ(ረህመሁሏህ) " ከየሁዳ እና ከነሷራ ጋር እበላለሁ፣ ከሙብተድዕ ጋር ግን አልበላም"
¢ኢማሙ አህመድ(ረህመሁሏህ) ለኻሊፋው ሙተዎክል እንዲህ አሉ "የሁዳን እና ነሷራን ሹም፣የብድዐ ሰዎችን አትሹም"
ማንቅያ:- የፉዳይሊን እና የኢማሙ አህመድን ንግግር የተመለከተ ሰው ምንድነው ይህን ያህል የብድዐ ሰዎች ከኩፍር የሚበልጥ ጥፋት አለባቸው እንዴ? ልል ይችላል። የዚህ ምላሽ :- ሰለፎች በብድዐ ሰዎች ላይ ይህን ያህል ከካፊሮች በላይ ያጠበቁት ስራቸው ከካፊሮች ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ወይም ከካፊሮች ኩፍር ይበልጣል ማለታቸው አይደለም። እነሱ የፈለጉበት የካፊሮች ኩፍር ግልፅ ስለሆነ ሙስልሞችን መሸወድ አይችሉም ወይም የመሸወዳቸው መጣን ዝቅተኛ ነው። የብድዐ ሰዎች ብድዐቸውን በሙስልሞች መካከል ቁርኣን ሀዲስን እየጠቀሱ የሚያሰራጩ ስለሆነ ከካፊሮች ይልቅ በቀላሉ ሙስልሞች በብድዐቸው መበከል ይችላሉ።ስለዚህ ጥፋታቸውን ከማሰራጫት አንፃር ከካፊሮች የከፉ ስለሆነ ሰለፎች በነሱ ላይ አጠበቁባቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ኩፍር የሚያደርስ ብድዐ መኖሩን መዘንጋት የለብንም።
የሰለፎች(የቀደምቶች) አቋም በብድዐ ሰዎች ላይ እንዲህ ከነበረ እኛም የሰለፎችን አቋም መከተላችን ለአማራጭ የሚቀርብ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታችን ነው። ለዚያም ነው ዑለሞች እንዲህ የሚሉት:-"وكل خيل في اتباع من سلف وكل شر في ابتداع من خلف"
" መልካም ነገር ሁሉ (በዲን) ቀደምቶችን በመከተል ነው፣መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ(በዲን) ዘግይቶ በመጡት ሰዎች ፈጠራ ነው"
ዑለሞች ይህንን ንግግር የበለጠ ግልፅ አርጎ የሚያስቀምጠው የሚሉት "الخير كل الخير في الاتباع والشر كل الشر في الإبتداع"
" መልካም ነገር ሁሉ (ሸሪዐ ያስቀመጠውን)በመከተል ነው፣ መጥፎ ነገር ሁሉ (ሸሪዐ ካስቀመጠው ውጪ) አድስ ፈጠራን በማምጣት ነው"
ሰለፎች(ቀደምቶች) ስብባል የሚፈለገው በመጥፎም በጥሩም ያለፉትን ሳይሆን በመልካም ያለፊትን ብቻ ነው የሚፈለግበት። እነሱም "ሰለፍ አስሷሊህ" በመልካም ቀዳሚዎች በመባል ይታወቃሉ።
#አሏህ ሆይ እነሱን ከንግግር እና ሙግት ባለፈ በተግባር ከተከተሉት አርገን፣የውመልቅያማም ከነሱ ጋር ሰብስበን ያ አሏህ!


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ሸይኽ ሙቅቢል(ረህመሁሏህ) እንደሚሉት እንደው ለሱና ስንል አፈር እንኳ እንብላ እንጂ የሰለፎችን መንገድ የሚሸራሪፉ ሰዎችን አንታገሳቸውም!!
#ኢልያስ አህመድ ይህንን ሙሐመድ አባታ የተባለን የኢኽዋን ቡድን አስተሳሰብ አራማጅ የሆነውን እና ደግሞ ከላይ እንደሚታዩት የመጅሊሱን ምክትል ፕሬዝዳንት የተበላሸ የሱፊያ የሽርክ መንገድ ተከታይ በመውሊድ ተዋቂ መሆኑን የሚያስተዋውቅ እና በዚም የሚኮፈስ የሆነን ግለሰብ ነው #ኢልያስ አህመድ በቻናሉ ፖስቱን እያሰራጨ የሚያስተዋውቅልን። ውድ ሰለፊዮች ዛሬ ላይ እንኳ በዚህ ሰው ልትሸውዱ አይገበም። አብዛኞቹ ሰለፊዮች ስለዚህ ሰው እና የጓዶቹ የመርከዙ ሰዎችን አቋም በተለያዩ መሻይኾች እና ዱዐቶች ማንቅያ አውቀው በተጠነቀቅ ላይ ነበሩ። ዛሬ ላይ ግን ትላንት በነዚህ ሰዎች ላይ ፍም እሳት ነክሰው ምላሽ ሲሰጡባቸው የነበሩ ሰዎች ዘወር ብለው ከነዚህ ከመርከዙ ሰዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መከላከልን እና ሹብሃ መጣልን ስለያዙ ትላንት በጠንካራ አቋም የነበሩ ፣በሰለፊያ ላይ የማይደራደሩ የነበሩ ወንድም እህቶች ራሱ ግራ ተጋብተው አላህ የጠበቃቸው ስቀር ከበፊት አቋማቸው እየወረዱ፣በመርከዙ ሰዎች ላይ ያላቸው አቋም እየተቀየረ መጥቷል። ዛሬ ላይ ግን ድፋዕ የሚደረግባቸው ሰዎች አቋም እንደ ቀን ፀሓይ ግልፅ ሆኗል። ድፋዕ የሚያደርጉም ቢሆን የመከለከላቸውን አቅም አስፊታው በድፍረት የበለጠ ግልፅ እያደረጉ ስለሆነ የነሱም ግልፅ እየሆነ ነውና ትላንት የተሸወድክ/ሽ ወንድሜ/እህቴ ዛሬ ላይ ግን አትሸወድ/ጂ!

✏️ሸይኼ/ኡስታዜ ወዳጄ ነው፣ ሀቅ ግን ከሱ በላይ ተወዳጅ ነው!
https://t.me/DaewaMinelKitabWosunnahInHalaba


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Forward from: የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
ወደሐይማኖቶች_አንድነት_የሚደረገው_ጥሪ_ግልጽ_ክህደት_ነው.pdf
895.6Kb
አዲስ መፅሐፍ

"الدعوة إلى وحدة الأديان كفر بواح"

"ወደሐይማኖቶች አንድነት የሚደረገው ጥሪ ግልፅ ክህደት ነው"

በሸይኽ ሑሴን ሙሐመድ አስ`ስልጢ -ሃፊዞሁሏህ-

#ከዓረበኛ ወደአማረኛ የተመለሰ

በቻልነው ሁሉ ለሌሎች እንዲደርስ የበኩላችንን እናበርክት

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

كن على بصيرة

https://t.me/alateriqilhaq


Forward from: የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
አልሐምዱሊላህ ሸይኻችን ሸይኽ ሐሰን ገላው ሃፊዞሁሏህ ከእስር ተለቀዋል

#የኢትዮጵያ_አህለሱና_ኢስላማዊ_ማህበር_ባ_ዳር


العلماء والقادة السلفيين الذين جاهدوا على إظهار الحق ودحض شبه المناهج الجديدة ونشر التوحيد والسنة في العالم وإطفاء ما يضادهما:

الشيخ ابن باز، والشيخ ابن عثيمين، والشيخ الفوزان، والشيخ ربيع المدخلي، والشيخ محمد أمان الإثيوبي ثم الهرري ثم الجامي، والشيخ الألباني ، والشيخ مقبل بن هادي اليمني الوادعي ، والشيخ صالح اللحيدان، والشيخ يحيى النجمي والشيخ حمدي بن عبد المجيد السلفي وغيرهم....
ሀቅን ግልፅ በማድረግ የአዳድስ ቡድኖችን ሹብሃ(ማጭበርበርያ) በማስወገድ ፣ተውሂድ እና ሱናን በዐለም በማሰራጨት፣የነዚህ ተቃራኒ የሆኑ ተግባሮችን በማጥፋት የታገሉ የሱኒዮች(የሰለፊዮች) መሪዎችና ዑሞች: -
ሸይክ ኢብኑ ባዝ፣ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን፣ሸይክ ፈውዛን ፣ሸይክ ረቢዕ አልመድኸሊይ፣ ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልኢትዮጲ አልሀረሪ አልጃሚ, ሸይክ አልአልባኒ፣ሸይክ ሙቅቢል አልየመኒ አልዋዲዒ ፣ ሸይኽ ሷሊህ አልሉሃይዳን፣ ሸይኽ የህያ አንነጅሚ ሸይኽ ሀምዲ ኢብኑ ዐብድል መጂድ እና ሌሎችም ...
تمسك بهؤلاء وأمثالهم حتى تثبت على عقيدتك وتسلم من شبهات الجديدة التي تبث صباحا ومساء بلباس الحق، وانظرها كنظرة الماء في الزجاجة كما نصح الإمام المجتهد المجدد ابن تيمية لتلميذه ابن القيم (رحمهما الله) بذلك تجاه الشبه.
በዐቂዳህ እንዲትፀና ጧት እና ማታ በሀቅ ስም ከሚሰራጩ ማዎዛገብያዎች ሰላም ትሆን ዘንዳ እነዚህን ዑለሞች እና አምሳያዎቻቸውን አጥብቀህ ያዝ! ልክ በብርጭቆ ያለውን ወሃ የሚትመለከተውን አይነት እይታ እዪ(ማለትም ለሚከሰቱ ማደናገሪያዎቹ ሁሉ እጅ እንዳትሰጥ) ታለቁ ታጋይ እምብዛው ልጠፋ የቀረበውን የሰለፎችን ጉዳና(ሱናን) አዳሽ የሆነው ኢብኑ ተይሚያ(ረህመሁሏህ) የተለያዩ ማደናገሪያዎችን አስመልክቶ ተማሪውን ኢብኑልቀይሚን(ረህመሁሏህ) በዚህ ምክር እንደመከረው አንተም በማደናገሪያዎች ሁሉ አትታለል። ቀደምት ሰለፎች ብሎም የቀደምት ሰለፎችን መንገድ ለዚህ ትውልድ ያስተላለፉት እነዚህ ታላላቅ ጀበሎች ምን ነበር አቋማቸው የምለውን እወቅ።


“ሀጂ ኢብራሂም - ከሙፍቲን ዑመር ይሻላል....(እንትና ከእንትና ይሻላል) " እያልክ አትዘናጋ። በጠላቶችህ ክፋት ልክ አንተም በጥንቃቄ ላይ ካልሆንክ የጉዳትህ መጠን የከፋ ነዉ የሚሆነዉ።

“የዝንጀሮ ቆንጆ የለዉም"፣ የጠላቶች ወንበር መቀያየር እንዳያደነዝዝህ! ሀጂ ኢብራሂምና ግብራበሮቹ ከዑመር ገነቴና ደጋፊዎቹ ይሻላሉ ብሎ የሚያስብ ካለ ራሱን ያታለለ ሰዉ መሆን አለበት።

ምክንያቶች:-

1ኛ ) ሀጂ የኢኽዋን አስተሳሰብ አራማጅ ነዉ። ኢኽዋን ደግሞ ከሌሎች ፍርቃዎች በብዙህ ጉዳዮች እንደሚከፋ ለማንም ግልፅ ነዉ።

2ኛ) ከኢኽዋንም የዋናዎቹን (የነሀሰን አልበና) እስተሳሰብ አለዉ። ለምሳሌ ሀጂ አደገኛ በሆነዉ “ወህደተል አድያን” (የሀይማኖቶች አንድነት) የሚያምን ሰዉ ነዉ። ይሄንንም በምስራቅ ሀረርጜ/ጭሮ ከተማ በተደረገዉ በአንድ ስብሰባ እንዲህ በማለት ግልፅ አድርጎታል። ⤵️

«የትኛዉንም ሀይማኖት ብትወስዱ መመለሻዉ ወደ ነቢ ኢብራሂም ነዉ። የትኛዉም ሀይማኖት! በጣም የሚደንቃችሁ በአለም ደረጃ ከተለያዩ ሀይማኖቶች የተወጣጡ ምሁራን የኢብራሂምያ ሀይማኖቶች (አይሁድ፣ ክርስቲያንና ኢስላም) ተብሎ አንድነት ለመፍጠር ተስማምተዋል።» ይላል‼️
ይሄ አስተሳሰብ ምን ያህል አደገኛና የኩፍር ንግግር እንደሆነ ካላወክ ምንም ሊረዳህ አልችልም!!!
[ልብ በሉ:- ሀጂ ይሄንን ሲናገር የምላስ መንሸራተት ወይም ድንግት የሰማዉን ወሬ አይደለም የተናገረዉ። “ከአለም ክፍል የተወጣጡ የሀይሞኖት ምሁራን የኢብራሂምያ ሀይማኖቶችን አንድነት ለማምጣት እየሰሩ ናቸዉ” ማለቱ ምን ያክል በጉዳዩ ተሳትፎ እንዳለዉ ነዉ የሚያሳየዉ። ይሄንኑ እዉነታ ሼይኽ ጣሃ ኸድር “የኢትዮጽያ ኢኽዋኖች እና ዋና ዋና መገለጫዎቻቸዉ” በሚል ርዕስ (በአፋን ኦሮሞ) በደረጉት ሙሓደራቸዉ ተናግረዋል።

3ኛ ) ሰለፊዮችን በቀጥታ ከማጥቃት ረገድ ሀጂ ከገነቴዉ ይከፋል። እስካሁንም በተጨባጭ ያየነዉም ይሄንኑ ነዉ። በዛዉ በጭሮ ስብሰባ ላይ እንዲህ በማለት በሰለፊዮችም ጭምር ዛቻ ሰንዝሯል:-
«ኦሮሚያ ዉስጥ ከኔ ፍቃድ ዉጭ ምንም አይነት የዳዓዋ እንቅስቃሴ ማድረክ አይቻልም፣ በኤን-ጂ-ኦ (NGO) ስምም ብሆን... » እያለ የሰለፊዮችንም እንቅስቃሴ ለመግታት ዝቷል።
ይሄንን ሊል የቻለዉ የመርከዝ “ጃሚዐቱ ሰለፊ” ሼይኽ አብዱልሀሚድ አወል በጭሮ አቅራብያ የሚገኝና በነሀጂ ኢብራሂም መሪነት ሲዘምቱበትና ሲያሳስሩ ሼይኹ በ“ኢትዮጵያ አህሉ ሱና ማህበር” ህጋዉነቱን ስያረጋግጡ ይሄንንም በማስፈራራት ሊያስቆሙ ማስፈራርያ ማድረጋቸዉ ነበር)። ሀጂ ኢብራሂም በኦሮሚያ በተለያዩ ቦታዎች ሰለፍዮች ለመታሰራቸዉ ከጄይላኒ ጋር ሆኖ ቀጥታ ትዕዛዝ የሚሰጠ እሱ ነዉ። ለዚህም በቂ ማስረጃ አለን!!!

ስለዚህ ሀጂ ኢብራሂም በአቂዳም ብሆን ከነዑመር ገነቴዉ የማይሻል፣ ሰለፊዮች ላይ ጥቃት ከምድረስ ደግሞ ከሱም የባሰ ሰዉ ነዉ። ዝም ብለህ “መጅሊስ ተስተካከለልን” ወዘተ እያልክ እትጃጃል!!! እነዚህ ምንም የማይፈይዱህ፣ (በሀቂቃዉም) የማይጎዱህ የዝንብ ስብስብ ናቸዉ። አንተ ትክክለኛ ጎዳና ላይ ከሆንክ የሚረዳህ አላህ ነዉ፣ ከዛህን በኃላ አብሮህ ያሉ የቀጥተኛ መንገድ ባለቤት ሙስልሞች ናቸዉ!!!
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
#ኸድር አቦምሳ


ሀጂ ኢብራሂም ማስፈራርያ ለሰለፊዮች:-

"አንዳንዴም NGO ሊሆን ይችላል (ኦሮሚያ ዉስጥ ዪዞ ለዳዓዋ የሚንቀሳቀሱት)። የፈለገ NGOም ብሆን በክልሌ ዉስጥ እኔ ስለሆንኩ የማስተዳድረዉ፣ የፈለገ ከፌዴራልም የሚመጣ NGO ብሆን ከኦሮሚያ የኢስላም ጉዳዮች ም/ቤት እውቅና እስካልተሰጠው ድረስ ቦታ የሌለው መሆኑን እንገልፃለን። በዚህ አጋጣሚ የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ሰላምና ፀጥታ አካላት ከጎኔ ይገኛሉ፣ ጉዳዩም ደርሰዋቸዋል ብዬ አስባለሁ "

#ኸድር አቦምሳ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


አድሱ የመጅሊስ ፕሬዝዳንት በሰለፊያ ላይ ከሚዘምተው ጀይላን የተሻለ መሆኑ ይቅርና ከሱም ይብሳል ተብሎ የሚታሰብ ግለሰብ ነው። ከታች የተገለፁ አቋሞቹ እና በሱንዮች ላይ የሚያደርጋቸው ጫናዎች ይህንን የሚያሳዩ ናቸው።
ሀጂ ኢብራሃም በ“ወህደቱል አድያን”/የሀይማኖቶች አንድነት/ የሚያምን ሰዉ ነዉ‼️

በቪዲዮዉ ላይ እንደሚትሰሙት እንዲህ ይላል
«ሀሉም ሀይማኖቶች በኢብራሂም ነዉ የሚገናኙት። ሁላቸዉም! እስኪ ዋናዎች ሀይማኖቶችን በሙሉ ዉሰዱ፣ የት ነዉ የሚገናኙት ካላችሁ ከኢብራሂም ሊያልፉ አችሉም። ሁላቸዉም በኢብራሂም ነዉ የሚገናኙት። 'የኢብራሂምያ ሀይሞኖቶች' ብለዉ አንድነት ለመፍጠርና የተረገዉ ምርምር ይደንቃችሃል። 'የኢብራሂምያ ሀይማኖቶች' ብለዉ በአለማቀፍ ደረጃ እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት.... (እናንተ ሱፊ-ሰለፊ እያላችሁ ትከፋፍሉናላችሁ)።

#ኸድር አቦምሳ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ዐረብኛን ብያንስ የሚትሞክሩ ወንድሞች እና እህቶች የዚህን ሸይኽ ሙሃደራዎቹን፣ፈትዋዎቹን ....አድምጡ!! በጣም ትጠቀማላችሁ።
ስማቸውን(شيخ محمد أمان الجامي) ብላችሁ በዩትዩብ ሰርች ካደረጋችሁ ታገኛላችሁ። ዐረብኛ መፃፍ የማትችሉ እዙህ በዐረብኛ የፃፍኩትን ስማቸውን ኮፒ አድርጋችሁ ሰርች ማድረግ ትችላላችሁ።

20 last posts shown.

139

subscribers
Channel statistics