Book Recommendation
የማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላት
የማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላት በ 1978 ዓ.ም በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት የታተመ መጽሃፍ ሲሆን የማርክሲዝም-ሌኒኒዝምም እርዮተ አለም ወደ አማርኛ ለመተርጎም በሚደረገው ስራ ላይ የርዕዮቱን ቃላት ፍቺ በማርኛ ለማስቀመጥ የሚሞክር ስራ ነው ። ምንም እንኳ የሶሺያሊዝምን ስርዓትን ለማስተማር የተቀመጠ መጽሃፍ ቢሆንም፣ ጥቅሙ ግን ከፍልስፍና፣ ከመዝገበ ቃላትና ከታሪክ አንጻር ከፍተኛ ነው ።
በዚህ መፅሐፍ የተነሳ ብዙ ሰዎች ከፍልስፍና ጋር ተዋውቀዋል። የእንግሊዝኛ የፍልስፍና ቃላትን ከግዕዝ ቃል እያመጣ አቻ ትርጉም የሚፈጥርበት መንገድ አስገራሚ ነው።
ለምሳሌ:-
* Metaphysics - ዲበ አካላዊ ፍልስፍና
* Empiricism - ዳሳሽነት
* Sensation - ሕውስታ
* Realism - እውንነት
* Positivism - ተጨባጫዊነት
* Phenomenology - ሥነ ክስተት
* Pantheism - ሁሉ አምላክነት
* Objectivism - ነባራዊነት
* Objective Truth - ነባራዊ እውነት
* Monism - አንዳዊነት
የመሳሰሉት። መፅሐፉ ከልቡ ዲክሽነሪ ነው። እነ ጋሽ ስብሐት ያሉበት ኮሚቴ እንዳዘጋጀው ይነገራል። The Best Philosophy Dictionary Book with a brief explanation for anyone who is interested in philosophy, it guides and use as a tool when we read any kind of philosophy books.
inbox me at https://t.me/yosefdibaba for the PDF file