Book Recommendation
ስለትናንሽ አለላዎች
ከዮናስ አ.
ምስሉን ሲያይ ውስጡ ለአፍታ ወንድሙ ትዝ አለው አሰበው ስለእሱ ማሰቡን እስካልተወ ድረስ ወንድሙ ውስጡ ሕያው ነው ሰው ብቻውን ሁለንታ ነው እያንዳንዳችን ውስጥ ህዋ አለ ልባችን ፀሐይ ነው በዙሪያቸው ደግሞ የምንወዳቸውን እናስቀምጣለን እንደረጨት የሚያስተዳድረን ገመድ ፣ የሚያያይዘን እርስ በርስ የምንተሳሰበው የትውስታ ነቁጦች ናቸው የሚያስታውሰው የሌለ ነገር ኹሉ ይሞታል፡፡ የማንሞተው ፣ ሕያው የምንኾነው….በምንተወው የትዝታ ዱካ ነው፡፡
ሊያይ ባይፈልግም መጥፎ ነገር አይቷል ጆሮዎቻችን እንዳይሰሙ ልንለግም እንችላለን ግን መስማታቸው አይቀርም፡፡ ሊሰማ ባይፈልግም ግን መጥፎ ነገር ሰምቷል እጆቻችን መዳሰስ ባይፈልጉም ስሜት ያስሳሉ እጆች የሚነኩት ፍለጋ አየር ላይ ተንከራተዋል፡፡
ከገዛ ራሳችን ስሜት የተፋታን መኾናችን አይገርምም ወይ? ሳንፈቅድ እንኖርና ሳንፈቅድ እንሞታለን፡፡ እየወደዱ መጥላት፣ እየፈለጉ መሸሽ፣ እየሄዱ መምጣት ፣ እየጠበቁ መተው ከባህላችን ጋር የተዋኻደው ለምንድን ነው ?
በጊዜ ኺደት ኹሉም ነገር የበለጠ ይመሰቃቀላል፡፡ ያለፍናቸውን ቀናት እንናፍቃለን፡፡ "ያ ደጉ ዘመን" ይባላል፡፡ "ልጅነቴ ልጅነቴ ማርና ወተቴ" ይባላል፡፡ ቀላል የሃይስኩል ፊዚካ ነው፡፡ Entropy ይባላል፡፡ ማለት እየፈረስን ይሁን እየተሰራን በጊዜ ኺደት ግን ቅርፅ እየቀየርን እንመጣለን፡፡ እና ትናንቶቻችን ያምራሉ ከዛሬዎቻችን የበለጠ ያልተዘበራረቁ ናቸው፡፡