Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር በነበረው የድብደባ ቪዲዮ ላይ ፖሊስ አስቀድሞ ምርመራውን አጠናቆ ለሚመለከተው አካል መላኩን ገለፀ።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭቶ በርካታ ሰዎችን ሲያስቆጣ በነበረው የድብደባ ቪዲዮ ላይ የፖሊስ አባላት አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ የምርመራ መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላካቸውን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል።
የከተማዋ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ቶማስ እሸቴ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩ ድርጊቱ የተፈፀመው ጥቅምት 14 ቀን 2018ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሲሆን ድርጊቱን የፈፀሙትና ተደብዳቢዋ አራት ጓደኛሞች ናቸው ብለዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው "ሀሜት አምተሻል" በሚል ምክንያት ተደብዳቢዋ ቤት ድረስ በመሄድ እንደሆነ የነገሩን ኮማንደር ቶማስ ፖሊስ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ከማህበራዊ ሚዲያው ስርጭት በፊት ምርመራውን ሲያጣራ እንደቆየና ተጠርጣሪዎቹም ለሶስት ሳምንታት ያህል በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲደረግባቸው እንደነበር ተጠቅሷል።
ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠትና ጥቆማ በማድረስ ላሳየው ተቆርቋሪነት ሊበረታታ እንደሚገባ ገልፀዋል።ድርጊቱ በህግ የሚያስጠይቅ በመሆኑ የሰዎችን መብት የሚያስከብሩ ህጋዊ አሰራሮች መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የድብደባ ድርጊቱ ህገ-ወጥ እንደሆነ ሁሉ፡ ምስሉን ቀርፆ በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት ህገ-ወጥነት በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል ብለዋል።እንዲሁም ወጣቶችና ታዳጊዎች በሚኖራቸው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው ላይ ወላጆችና ቤተሰቦች አስፈላጊውን ክትትልና ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ መክረዋል።
@darashMedia