Darash Media


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ፣️‼️ትክክለኛው ቻናል ይሄ ብቻ ነው።
ይህን ቻናሌን ለሌሎች ሰዎች ሼር አድርጉ።
#አመሰግናለሁ🙏

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


እጅግ አሰቃቂ አደጋ በአዲስ አበባ ደረስዋል‼️
ማለዳውን 1:50 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡

የጉዞ አቅጣጫው ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ የሆነ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-05997 ትግ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል የ5 ወንዶችና 1 ሴት ህይወት አልፏል፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

@darashMedia
@darashMedia


በዚህ አመት 12.8% በመቶ የሚሆኑት አልፈዋል


የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በላከልን መረጃ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ ከሰዓት በኋላ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቅሷል።

በዓመቱ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 62 በመቶ የሚሆኑት በኦንላይን ፈተናውን ወስደዋል።

በ2018 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ 563 ሺህ 501 ተማሪዎች በ607 የፈተና ማዕከላት ውስጥ የተፈተኑ ሲሆን ፈተናው በ6 ዙሮች ተሰጥቷል።

ከዘንድሮ ጠቅላላ ተፈታኞች መካከል 306 ሺህ 456 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ 257 ሺህ 45 ደግሞ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ነበሩ፡፡

ውጤቱን በተመለከትም ትምህርት ሚኒስቴር በ9 ሰዓት መግለጫ እሰጣለሁ ብሏል፡፡

@darashMedia
@darashMedia


እዚህ ፎቶ ላይ ያለው ልጅ ደረቱ ላይ ያለውን ፅሑፍ ልብ በሉ! 😱 ከዛም የሆነውን ስትሰሙ በእጅጉ ትደነቃላችሁ!

ታዋቂው አርቲስት እንግዳሰው ሀብቴ (ቴዲ) በአርባምንጭ በ220 ሺህ ብር የገዛውን የቅርብ ጊዜ Samsung Ultra ስልኩን መንገድ ላይ ጥሎት ነበር!

ነገር ግን ይህ ውድ ስልክ የወደቀው መልካምነትና ታማኝነት በታደለው ሙሉቀን በተባለ የአርባምንጭ ወጣት እጅ ነበር! አርቲስት ቴዲና ባልደረቦቹ ደውለው ስልኩ እንደወደቀባቸው ሲነግሩት፤ የወጣት ሙሉቀን መልስ የብዙዎችን ቀልብ የሚስብ ነበር!

በኛ(ጋሞ) ባህል የሰው እቃ መውሰድ ጎሜ ነው!' በማለት ያለበትን ቦታ ጠቁሞ የ220 ሺህ ብር ስልኩን ለአርቲስት ቴዲ በሙሉ ታማኝነት አስረክቧል! በመፅሐፈ ምሳሌ '
ልጄ ሆይ ህጌን አትርሳ

' እንደሚለው፤ የወጣቱ ደረት ላይ ያለው ፅሑፍና ተግባሩ በትክክል ተገጣጥመዋል!"

ለአባቶች መልካም ባህልና እሴት ቅድሚያ ለሰጠው፤ ቃሉን ደረቱ ላይ ብቻ ሳይሆን ልቡ ላይ ጭምር ላተመው ለወጣት ሙሉቀን ምን አስተያየት አላችሁ? ኮሜንት ላይ አጋሩኝ።

@darashMedia
@darashMedia


አቶ ኢሳያስ ጂራ ብቸኛ እጩ ሆነው ቀርበዋል !

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መስከረም 5/2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴው እጩዎችን እስከ ነሀሴ 4/2018ዓ.ም ድረስ መመዝገቡን ገልጿል።

ኮሚቴው ነሐሴ 5 ፣ 11 እና 13 ባደረጋቸው ስብሰባዎች የቀረቡ እጩዎችን ሰነድ የምርመራ እና የማጣራት ተግባር አከናውኗል፡፡

በዚህም መሠረት ለዕጩ ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪነት የቀረቡት ብቸኛ ተወዳዳሪ አቶ ኢሳያስ ጅራ ቦሾ መሆናቸውን አሳውቋል።


ግን እስከመቼ ነው ህዝብ መቀለጃ የሚሆነው?

@darashMedia
@darashMedia


የአገራዊ ምክክሩ አራት አጀንዳዎች ከስምምነት ሳይደረስባቸው ወደ ቀጣይ ዙር ተሻገሩ❗❗

በአገራዊ ምክክሩ የመንግሥት አደረጃጀትን ጨምሮ አራት አከራካሪ ጉዳዮች በ120 አባላት ያለው የሐሳብ አዘጋጅ ቡድን ስምምነት ሳይደረስባቸው ወደ ቀጣዩ የምክክር ሂደት መሻገራቸው ተገለጸ።

በአጀንዳው 500 ተሳታፊዎች ባሉበት የሥራ ቡድን 53 ጉዳዮች ቀርበው፣ 50 ላይ ስምምነት ሲደረስ ሦስቱ ግን ሳይስማሙ እንደቀሩ ቀደም ሲል ተገልጿል። የሐሳብ አዘጋጅ ቡድኑ እነዚህን ጉዳዮች በማጣጣም 62 ምክረ ሐሳቦች አድርጎ ሲያቀርብ፣ አራቱ ላይ የጋራ ስምምነት ሊደረስ እንዳልቻለ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

ከእነዚህ መካከል ዋነኛው የመንግሥት አወቃቀር ጉዳይ ሲሆን፣ አንደኛው አማራጭ ፓርላሜንታዊ ሥርዓት እንዲኖርና ፕሬዚዳንቱ ከፓርላማ እንዲመረጥ የሚደግፍ ሲሆን፣ ሌላኛው ፕሬዚዳንታዊ ሥርዓት እንዲኖርና ፕሬዚዳንቱ በሕዝብ ቀጥታ እንዲመረጥ የሚል ነው።

ሌሎቹ ሁለት ጉዳዮች የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት አመራረጥና በምክር ቤቱ የብሔረሰቦች ውክልና አሠራርን የሚመለከቱ ናቸው። በአባላት አመራረጥ ላይ አንዱ ሐሳብ አባላት በክልሎች ምክር ቤቶች እንዲመረጡ ሲደግፍ፣ ሌላው ሕዝቡ በቀጥታ እንዲመርጣቸው የሚል ነው።

በብሔረሰቦች ውክልና ላይም አንድ ሐሳብ በሕዝብ ብዛት መሠረት ተጨማሪ ውክልና እንዲኖር ሲደግፍ፣ ሌላው ሁሉም ብሔረሰቦች በእኩል መልኩ እንዲወከሉ የሚል ሐሳብ ቀርቧል።

አራተኛው አከራካሪ ጉዳይ “ውህድ ማንነት” የሚለው ሐሳብ ሲሆን፣ የሥራ ቡድኑ ቀደም ሲል በስምምነት አልፎ የነበረው ሐሳብ በ120 አባላት ባለው የሐሳብ አዘጋጅ ቡድን ዳግም የአለመስማማት ጉዳይ ሆኗል። በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ መቅረቡንና ከስምምነት ይልቅ አለመስማማት በሚል ወደ ቀጣዩ ዙር መተላለፉን ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

በመሆኑም አራቱ ጉዳዮች በቀጣዩ የምክክር ዙር የበለጠ ውይይትና የመግባባት ሥራ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሆነው መቀጠላቸው ታውቋል።

@darashMedia
@darashMedia


በተወዳጁ ቻናላችን ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ???

ያናግሩን👇
@Dershsupport
@Dershsupport
👆 ማስታወቂያ ለማሠራት


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር በነበረው የድብደባ ቪዲዮ ላይ ፖሊስ አስቀድሞ ምርመራውን አጠናቆ ለሚመለከተው አካል መላኩን ገለፀ

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭቶ በርካታ ሰዎችን ሲያስቆጣ በነበረው የድብደባ ቪዲዮ ላይ የፖሊስ አባላት አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ የምርመራ መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላካቸውን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል።

የከተማዋ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ቶማስ እሸቴ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩ ድርጊቱ የተፈፀመው ጥቅምት 14 ቀን 2018ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሲሆን ድርጊቱን የፈፀሙትና ተደብዳቢዋ አራት ጓደኛሞች ናቸው ብለዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው "ሀሜት አምተሻል" በሚል ምክንያት ተደብዳቢዋ ቤት ድረስ በመሄድ እንደሆነ የነገሩን ኮማንደር ቶማስ ፖሊስ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ከማህበራዊ ሚዲያው ስርጭት በፊት ምርመራውን ሲያጣራ እንደቆየና ተጠርጣሪዎቹም ለሶስት ሳምንታት ያህል በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲደረግባቸው እንደነበር ተጠቅሷል።

ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠትና ጥቆማ በማድረስ ላሳየው ተቆርቋሪነት ሊበረታታ እንደሚገባ ገልፀዋል።ድርጊቱ በህግ የሚያስጠይቅ በመሆኑ የሰዎችን መብት የሚያስከብሩ ህጋዊ አሰራሮች መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የድብደባ ድርጊቱ ህገ-ወጥ እንደሆነ ሁሉ፡ ምስሉን ቀርፆ በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት  ህገ-ወጥነት በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል ብለዋል።እንዲሁም ወጣቶችና ታዳጊዎች በሚኖራቸው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው ላይ ወላጆችና ቤተሰቦች አስፈላጊውን ክትትልና ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ መክረዋል።

@darashMedia
@darashMedia


ትራምፕ ካይሮንና አዲስ አበባን ማስታረቅ ይፈልጋሉ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የዓረብ እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቦውሎስ እንዳሉት፤ ዶናልድ ትራምፕ በናይል ወንዝ ተፋሰስ አገሮች መካከል የውሃ አጠቃቀም ስምምነት እንዲደረስና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውዝግብ እንዲፈታ ካይሮንና አዲስ አበባን ማስታረቅ ይፈልጋሉ።

ዋሽንግተን ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎችን እንደምትፈልግ እና ከሁሉም ወገኖች ጋር ንግግሮች መቀጠላቸውን የገለጹት አማካሪው፣ ግብፅና ኢትዮጵያ ሁሉንም አገሮች የሚያረካ ስምምነት ላይ ለመድረስ በውይይት እንዲሳተፉ አሜሪካ ማበረታታቷን እንደቀጠለች ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በታሪካዊ የናይል ውሃ ስምምነቶች ዙሪያ ስላሉት ውዝግቦች፤ ዋሽንግተን የሦስቱ አገሮች ባለሙያዎች በጋራ በመሥራት ለተነሱት ቴክኒካዊ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ ታበረታታለች ብለዋል።

አሜሪካ ለሁሉም ወገኖች ቴክኒካዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ባለሥልጣኑ አረጋግጠዋል።

@darashMedia
@darashMedia


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ😭😢

ልጆቹ ለህግ ሊቀርቡ ይገባል

@darashMedia
@darashMedia


ሀግሬ ቲቪ በገፃቸው...

"አዲስ ነገር ከሀገሬ ቴሌቪዥን!"

ከዚህ በፊት ሀግሬ ቲቪ የተመረጡ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ሲያስተላልፉ ነበር...

ምን አልባት ፕሪሚየር ሊግ....

@darashMedia
@darashMedia


በተወዳጁ ቻናላችን ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ???

ያናግሩን👇
@Dershsupport
@Dershsupport
👆 ማስታወቂያ ለማሠራት


የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምላሽ

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዘውዱ ሃፍቱ በጉዳዩ ላይ የቀረቡለትን ሰነዶችና ማስረጃዎች በመመርመር ነፃና ገለልተኛ ውሳኔ መስጠቱን አስታውቋል።

ፍርድ ቤቱ በሰበር ሰሚ ችሎት መቅረብ የሚገባቸው ማስረጃዎች እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ትዕዛዝ መስጠቱንና ዕድል መስጠቱን ገልጿል።

እንዲሁም መሰማት የሚገባቸውን ምስክሮች በመስማት ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው ውሳኔ ተከሳሾቹ በነፃ እንዲለቀቁ መወሰኑ በሕጋዊ ሂደት የተደረገ መሆኑን አስረድቷል።

በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያለው አካል ጉዳዩን ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በማቅረብ በሕጋዊና ገንቢ መንገድ ሐሳቡን ማቅረብ እንደሚችልም ፍርድ ቤቱ ገልጿል።

ከዚህ ውጪ በፍርድ ቤት ላይ ጫና ማሳደር ተቀባይነት እንደሌለው ያስገነዘበው ፍርድ ቤቱ፣ ጉዳዩ ሕጋዊ ሂደቱን ተከትሎ የመጨረሻ ውሳኔ ካገኘ በኋላ በመገናኛ ብዙኃን ላይ ተጨማሪ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

 @darashMedia
@darashMedia


ሀገር ከፍተኛ በጀት በጅታ ልጆቿ ሲመክሩ ዛሬም በጫካ ጦር አንግበው ከመንግሥት ጋር የህዝብን ሠላም የሚነሱ አሉ። እኛ እንደ ህዝብ ፕሬዝዳንት ሳይሆን የሚያስፈገን ዳቦና ሠላም ነው።

አዲስ አበባ እና ፊንፊኔ የሚሉ ሁለት ቃላት በሃሳብ አሟገቱን እንጅ መች አጣሉን። ብልፅግና በሩን ዘግቶ ቢመክር ምን ጥቅም?

እኛ እንደ ህዝብ እውነተኛ ምክክር ነው የሚያስፈልገን

ህውሃት
ፋኖ
ኦነግ
ኦብነግ እና ሌሎችም ታጣቂዎች ዛሬም በየአካባቢው ከመንግሥት ሃይሎች ጋር የህዝብን ሠላም እየነሱ የምን ምክክር ነው። ብልፅግና ከራሱ ጋር ሳይሆን ከነዚህ ሃይሎች ጋር ነው መምከር ያለበት።

ብልፅግና ብቻውን መክሮ ሀገር የሚለወጥ ቢሆን 8 አመት ከበቂ በላይ ነበር። ስለዚህ ምምሩ ለይስሙላ የመንግስትን አጀንዳ ለማስፈጸም ሳይሆን እውነተኛ የሃገር መታረቂያ መሆን አለበት!

@darashMedia
@darashMedia


የምክክር ኮሚሽኑ ከመጀመሪያው ሲመሠረት በብዙዎች ሲፈራ የነበረው የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ነበር።

ባለፉት ሳምንታት ምክክሩ ሲጀመርም ኮሚሽኑ የመንግስትን ሁለት ዋና ተልዕኮዎች ለማስፈፀም ነው የተቋቋመው በሚል ብዙዎች እየተናገሩ ነበር። አሁንም ያ በግልጽ እየታየ ነው።

@darashMedia
@darashMedia


በአዲስአበባ ጉዳይ ተወሰነ

አከራካሪ የነበረው የአዲስ አበባ ጉዳይ ስምምነት እንደተደረሰበት ተገለጸ

በተመካካሪዎች ዘንድ በሰፊው አከራካሪ ከነበሩ አጀንዳዎች መካከል የፌደራል ከተሞች፡- የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ጉዳይ ዋነኛው ሲሆን፣ በዛሬው የምክክር ውሎ በአጀንዳው ላይ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ተገልጿል።

ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ በተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 4 ሺህ ተመካካሪዎች በተመረጡ 8 አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ መቆየታቸው ይታወቃል።

በዛሬው የምክክር ጉባኤ ውሎ በተመካካሪዎች ዘንድ በሰፊው አከራካሪ የነበረው የፌደራል ከተሞች፡- የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ጉዳይ አጀንዳ ስምምነት እንደተደረሰበት ታውቋል።

በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ እንድትሆን 500 አባላት ያሉት የተመካካሪዎች ቡድን ተስማምተዋል።

ልዩ ጥቅምን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች በቀጣይ በሰፊው እንደሚመከርባቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ጉዳይ በተመካካሪዎች ዘንድ በሁለት ጎራ፤ «የኦሮሚያ ክልል አካል እና ዋና መቀመጫ ትሁን» በሚል እና «የፌደራል ከተማ ዋና መቀመጫ ትሁን» በሚል በተመካካሪዎች ዘንድ ለቀናት ሲያጨቃጭቅ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

@darashMedia
@darashMedia


ክልሉ ግድያውን አስተባብሏል‼️
ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት ግልሰቦች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ መገደላቸው ይታወሳል።

ይህንን አስመልክቶ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ መግለጫ የሰጠ ሲሆን
'እርምጃ የተወሰደባቸው ግለሰቦች የጦር መሳሪያ በመታጠቅ በግድያ ላይ የተሰማሩ እና በመንግሥት ፀጥታ አካላት ላይ ጭምር ጉዳት ያደረሱ አካላት እንደነበሩ እና በትክክል የተረጋገጠባቸው ሽፍታዎች ናቸው ብለዋል።

በመሆኑም በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች የመንግስትን የሰላም አማራጮችን አንቀበልም ባሉ ሽፍታዎች ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ነው ያሉት።

የሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃ  በማስረጃ ያልተደገፈ እንዲሁም ክልሉን የማይመጥን እና የህዝቦችን የእርስበርስ አንድነትን የሚሸረሽር እንደሆነም ገልፀዋል።

መንግስት የህዝብን ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚወስደው እርምጃ ብሔር ተለይቶ የሚወሰድ እርምጃ ተብሎ በሀሰተኛ ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ እንደሆነም ገልፀዋል።

እነዚህ ሽፍታዎች የጦር መሳሪያ በመታጠቅ በግድያ ላይ የተሰማሩ እና በመንግሥት ፀጥታ አካላት ላይ ጭምር ጉዳት ያደረሱ አካላት እንደነበሩ እና በትክክል የተረጋገጠባቸው ሽፍታዎች ናቸው'ብለዋል።

ግለሰቦቹ ወንጀል ሰርተው ቢያዙ እንኳን በአደባባይ ይረሽኑ የሚል የህግ ማዕቀፍ አለ? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።

ክልሉ ቤተሰቦቻቸው ላይም ግድያውን እንዲያስተባብሉ ጫና እያደረገባቸው እንደሚገኝ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት ዘግቧል።

@darashMedia
@darashMedia


በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ብሔርን መሰረት ያደረገው የክልሎች አወቃቀር ይቀጥል በሚለው የ500 ቡድን የሀገራዊ ምክክር ተመካካሪዎች ተስማምተዋል፡፡

አገሪቱ የምትከተለው የመንግስት ሥርዓት ምን ይሁን? ለሚለው ተመካካሪዎቹ ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት ትመራ በሚለው ላይ ሙሉ ለሙሉ ተስማምተዋል ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ ከየት ይመረጥ? ሥርዓቱ ፓርላምታዊ ሆኖ ከፓርላማ ይመረጥ? ወይስ ሙሉ በሙሉ ሥርዓቱ ፕሬዚዳንታዊ ሆኖ በህዝብ ቀጥታ ይመረጥ የሚለው ግን ሁሉምን አስማሚ አልሆነም ፡፡

በዚህም በመንግሥት አደረጃጀት እና ቅርፅ በፖለቲካ ሥርዓት፣ ውክልና የምርጫ ሥርዓት ስር ሲመከር የሰነበተው ተመካካሪ ቡድን እነዚህ አጀንዳዎች በልዩነት ወደ ቀጣይ ምዕራፍ እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ውክልና ምን ይምሰል? የሚለውም ሌላው በልዩነት ያለፈ ንዑስ አጀንዳ ነው፡፡

@darashMedia
@darashMedia


Forward from: ጎህ አስጠኚ
​✨ ጎህ አስጠኚ | Goh Tutoring ✨
ወላጆች ልጆቻቹህ ለ2019 የትምህርት ዘመን ዝግጁ ናቸው?


📚 ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ የቀረበ ልዩ የኦንላይን (Online) የማስጠናት አገልግሎት!

​🌟 ከእኛ ጋር ሲማሩ የሚያገኙት ልዩ ጥቅሞች፡
​🖥️   በኦንላይን ቀጥታ (Live) ከተማሪዎች ጋር በመገናኘት የሚሰጥ ትምህርት

​📝  ለብሔራዊና ለትምህርት ቤት ፈተናዎች የሚያዘጋጁ በርካታ የልምምድ ጥያቄዎች

​📊   በየክፍል ደረጃ  መደበኛ የክለሳ ፈተናዎች

​📑   በአጭሩ የተዘጋጁ እና በቀላሉ የሚገቡ አጋዥ ማስታወሻዎች (Short Notes)

​❓ ያልገባቸውን ርዕስ ወዲያውኑ አስተማሪውን ጠይቀው የመረዳት ዕድል

​🎯  ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞች ልዩ ትኩረትና ዝግጅት!

​💰 የክፍያ መጠን

​👥 በቡድን (በአንድ ግሩፕ 5 ተማሪዎች ብቻ)፡

👉በሳምንት 3 ቀን  Live class

​ከ5ኛ - 8ኛ ክፍል፡ በወር 1,100 ብር ብቻ
​ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል፡ በወር 1,500 ብር ብቻ

​👤 በግል (Private - 1 ለ 1)፡

​ከ5ኛ - 8ኛ ክፍል፡ በሰዓት 200 ብር
​ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል፡ በሰዓት 250 ብር

ቀድመው ለሚመዘገቡ ተማሪዎች መደበኛው ጥናት ከመጀመሩ በፊት ነፃ የ 15ቀን ጥናት እንሰጣለን!

​📲 አሁኑኑ ይመዝገቡ!
📞 ስልክ፡
0914296774 / 0703923311
💬 ቴሌግራም፡
@Gohtutoring


የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ  የኃይል አቅርቦት

ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፡-

ከጠዋቱ 2፡00-11፡00

👉ጎፋ ካምፕ ኮንዶሚኒየም ፣ ጀርመን አደባባይ ፣ ጉራጌ ሰፈር፣ ትግሬ ሰፈር፣ ካፍ ነዳጅ ማደያ እና አካባቢው ፣

👉 ሀዋርያው ቸርች ፣ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ፣ መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ ፣ ቆሬ አደባባይ፣አሚጎ ኮንዶሚንየም ፣ ፋና ት/ቤት ፣አርሴማ ቤ/ክ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ጀርመን አደባባይ እና አካባቢው ፣

👉ባህርዳር ቀበሌ11፣ቴሌ፣ምድረገነት፣ አዲሱ  አስፓልት፣ ቀበሌ14፣ ልደታ፣ ይባብ፣ ባታ፣100ካሬ፣ ኮቲና፣ሙሉጌታ ሪልስቴት፣ አቡነሃራ፣ ዱዱ፣ ጨለንቆ፣ ቀርሳ፣ ቆሎሚ፣ ቁልቢ እና አካባቢው ፣

👉ድሬ ከአስፋልት በታች፣ ጉዳ፣ ኬላ፣ ጉዮ፣ ታጠቅ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ቶልቻ ፣ ሰሪፊ ፣ ጉጄ ፣ ቶልቻ ፣ ታጠቅ ኢንዱስትሪ ፣ ፌስቱላ ማዕከል እና አካባቢው፣

👉ኮተቤ ኮሌጅ  ፣ መሳለሚያ ፣ ኮተቤ አማኑኤል ሆስፒታል ፣ ዘርፌ ቦኖ ፣ ፍናን ዶቦ ፣ ቀርሳ ሚካኤል እና አካባቢው፣

👉ጥሩ መናፈሻ፣ አባዶ ኮንዶሚኒየም በከፊል፣ጣፎ አያት ኮንዶሚንየም ፣ ሳራ አምፓል ፣ኮተቤ ካራ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 2፡00-9፡30

👉ቀራንዮ መድህንዓለም ቤ/ክ ፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ ፣ መስኪድ ፣ ቤተል ፓስታ ቤት ፣ኮልፌ ወ.8  እና አካባቢው

👉ሆላንድ ኤምባሲ፣ የሺ ደበሌ፣ ጦርሀይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ፣ ቻይና ኢንባሲ፣ አጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን፣ አባ ጅፋር መስኪድ እና አካባቢው፣ 

👉ግራር ኮንዶሚኒየም ፣ አለምባንክ ፣ ትሮፒካል ፣ አየር ጤና ኪዳነ ምህረት ፣ ጣፎ ገብርኤል ፣ ገመናይ ማርያም እና አካባቢው፣

👉ካራ ፣ ናትራን ፣ ለማ ነጎ ት/ቤት ፣ አየር ጤና ፣ አየር ጤና ኪዳነምሕረት ፣ አየር ጤና ሞቢል ፤ ፉሪ ፣ ሰይድ ያሲን ጀርባ፣ ኡራኤል  እና አካባቢው ፣

ስለሆነም በአካቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

@darashMedia
@darashMedia

20 last posts shown.