🕋
የረመዷን ሌቦች📌
እንደሚታወቀው አላህ ከሰፊ እዝነቱ ለባሮቹ በተለያዩ ወቅቶች ወደ እርሱ ሊመልሳቸው የሚያስችላቸውን የዒባዳ ድግስ አዘጋጅቶላቸዋል ከነዚህ የአምልኮ ድግሶች ውስጥ ይህ ከፊታችን እየመጣ ያለው የበረካ ወር ረመዷን ነው። በዚህ ወር ላይ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ የተለያዩ አምልኮዎችን ልናደርግ ይገባል ይህ ወር አላህ ላደረሰው ትልቅ እድል ነው። ኢማናችንን ምናድስበት የተለያዩ ተጓዳኝ ሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ከጠነከሩ የሚያገግሙበት ሰላት መስገድ ሚከብዳቸው አካሎች የሚለማመዱበት ሰደቃ መስጠት የማይሆንላቸው ስስት ያለባቸው ሰዎች መስጠትን የሚለማመዱበት ሌሎችም መልካም ነገራቶች የሚተገበሩበት ውድ እጅግ በጣም የተከበረ ወር ነው።
ታዲያ በዚህ ወር መፆም ፣ቁርኣን ማንበብ፣ ሌሊት መቆም፣ ዚክር ማብዘት፣ ዘመድ መዘየር የታመመ መጠየቅ ሌሎችም መልካም ነገሮች ላይ ማተኮር ሲገባን በሌላ መጥፎ ነገራቶች ተወጥሮ ረመዷንን ከስሮ ማሳለፍ የለብንም❗️
ሰለፎች በረመዷን ወር ቁርኣን ማንበብን ያበዙ ነበር ከፊሎቹ በየቀኑ ያኸትሙ ነበር ከፊሉ በየ ሶስት ቀኑ ያኸትማል ። ባጠቃላይ ይህን ወር በዒባዳ ተወጥረው ነበር የሚያሳልፉት።
ረመዷንን ልንጠቀምበት ይገባል ረመዷናችንን ሊሰርቁቁን ከተዘጋጁ
ሌቦች ልንጠብቀው ይገባል።
አንደኛው የረመዷን ሌባ
📲ስልክ ይህ ስልክ በረመዷን ወቅት የሆነ መፍትሄ ካላበጀህለት እንደፈለክ ምትጠቀመው ከሆነ ትከስራለህ ምክንያቱም አላህ ካንተ ሚፈልገው መራብህን ወይም መጠማትህን አይደለም❗️ሚፈለገው ሁሉ ነገርህ እንዲፆም ነው አይንህ፣ ጆሮህ፣ ምላስህ ሁለመናህ ከሀራም መጠበቅ አለበት። ብዙ ሰዎች ስልክ አጠቃቀማቸው የተበላሸ ነው በዚህ በተከበረ ወር ወንዱ ከሴት ጋር ማውራት ሴቷ ከወንድ ጋር ማውራት፣ ቲክቶክ መጠቀም፣ ሌላም ሌላም ነገራቶችን ማየት ለውርደት፣ ለኪሳራ ይዳርጋል። ነብዩ አንድ ጊዜ ሚንበር ላይ ሆነው አሚን አሚን አሚን አሉ። ከዛም ለምን አሚን እንዳሉ ሲጠይቋቸው እንዲህ አሉ፦ ጅብሪል መጥቶ እንዲህ አለኝ፦
ረመዷንን አግኝቶ ምንም ሳይጠቀምበት ወንጀሉ ሳይማርለት ረመዷን የሄደበት ሰው አፍንጫው ከአፈር ይቀላቀል ወይም የተዋረደ ይሁን ከዛም ነብዩን አሚን በል አላቸው አሚን አሉ።
ዱዓ አድራጊው ጂብሪል አሚን ያሉት ነብዩ صلى الله عليه وسلم
አደጋ ውስጥ ልትገባ ትችላለህና በዚህ ወር ላይ ስልክ አጠቃቀምህን ባህሪህነን እሳምር❗️
ይቀጥላል…
👉
https://t.me/AbuEkrima