መኑ ውእቱ ገብርኄር?
ቸር አገልጋይ ማነው?
የዓቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት > ይባላል።
ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ሲሆን በዚህ ቀን ስለ ቅን አገልጋዮች፣ ለአገልጋዮች የሚያገለግሉበት ጸጋ የሚሰጥ ወኃበ ጸጋ አገልጋዮቹን > እያለ ዋጋ የሚሰጥ አምላክ መሆኑ እየታሰበ ይመለካል።
ቸር አገልጋይ (ገብርኄር) ማቴ ፳፭፤፲፬-፴ በዚህ ዕለት በቅዳሴ ሰዓት የሚነበበው ቃል ወንጌል እንዳመለከተን መድኃኒታችን የወንጌልን አደራ በምሳሌ እንዳስተማረ ተገንዝበናል። ትምህርቱም አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር። ወደ ሩቅ አገር ለመሄድ ባሰበ ጊዜ አገልጋዮቹን ጠርቶ ከመንገዱ እስኪመለስ ድረስ ይሰራበት ዘንድ ለአንዱ አምስት መክሊት፣ ለሁለተኛው ሁለት፣ ለሶስተኛውም አንድ መክሊት(ታለንት) ሰጣቸው።
አምስት መክሊት የተቀበለው ወጥቶ ወርዶ ሌላ አምስት መክሊት በማትረፍ አሥር መክሊት አደረገው። ሁለት መክሊት የተቀበለው ወጥቶ ወርዶ እጥፍ አትርፎ አራት መክሊት አደረገው። አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት በልቡ ውስጥ ስጋት፣ ጥርጥርን፣ ፍርሃትንና አለማመንን ስላነገሠ ስሰራበት ቢጠፋብኝስ? ቢሰርቁኝስ? ቢቀሙኝስ? እያለ በማሰብ እሰራለሁ ብዬ ያለኝን ከማጣ ለምን ደብቄ አስቀምጬ በመቆየት ሲመጣ የሰጠኝን አልመልስም ብሎ መክሊቱን ቆፍሮ ቀበረው። ጊዜው ሲደርስ ባለንብረቱ መጣና አገልጋዮቹን ይተሳሰባቸው ጀመር።
በቅድሚያ አምስት የወሰደው መጣና
> ብሎ አሥር መክሊት ለጌታው ሰጠ። ጌታውም
> አለው።
ሁለተኛው፣ ብሎ እጥፍ ማትረፉን ገለጾ ለጌታው አስረከበ። እንደባለ አምስቱ ተባለ።
ሦስተኛው፣ መጣ ሰነፍ ቃሉም መራራ ነው። የሰነፍ አካሉም ብቻ ሳይሆን አእምሮውም ሰነፍ ነው። ጌታው ገንዘቡን ሲጠይቀው፣ ይህንን የማይረባ አገልጋይ ግን ልቅሶ፣ ጥርስ ማፏጨት ወዳለበት ጽኑ የፍርድ ቦታ ውሰዱት አለ ይላል በምሳሌ የተሰጠው የመድኃኒታችን ትምህርት። የትምህርቱም ትርጉም እንደሚከተለው ነው።
የንብረቱ ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሦስቱ አገልጋዮች ልዩ ልዩ ጸጋ ተሰጥቶአቸው ያሉ ህዝበ ክርስቲያኖች ምሳሌዎች ናቸው። ስጦታው በአኃዝ ሲታይ ልዩነት መኖሩ አንዱ ጸጋ ከሌላው የሚለይ መሆኑን ያሳያል።
የአገልጋዮቹ ባሕርይ
፩) የመጀመሪያው እና የሁለተኛው አገልጋዮች መንፈስ ሁለቱም ሰርቶ ማግኘት እንደሚቻል የሚያምኑ፣ ለጌታቸው ታማኞች፣ በስራ ላይ የሚያጋጥማቸውን ችግር በማሰብ ጊዜአቸውን የማያጠፉ ናቸው። ሁለተኛው አገልጋይም እንደ መጀምሪያው አገልጋይ ለምን አምስት አልተሰጠኝም ብሎ ያለኩርፊያ በተሰጠው የሚሰራ ነው። ባለአምስቱ አምስት ሲያተርፍ ባለሁለቱም ሁለት በማትረፍ ተመሳሳይ ትጋት የታየባቸው አገልጋዮች ናቸው። ዋጋቸውም እኩል ነው ያገኙት። ለሁለቱም የተሰጠው የክብር ስም አንድ ነው። ገብርኄር (ቸር አገልጋይ) የሚል የገቡበትም የክብር ስፍራ አንድ ነው። ያም ነው። ሁለቱም በጥቂቱ የታመኑ ነበሩ። ከሰጪው አንጻር ሲታይ የባለ አምስቱም እንደ ባለ ሁለቱም፣ የባለሁለቱም እንደ ባለአምስቱ ጥቂት ነበር። ሰው በተሰጠው ሳያንጎራጉር ፈጣሪውን ቢያገለግል ክብር ያገኛል። ለሰው ልጅ የሚጠቅመው ችሎታውን፣ ጸጋውን መቁጠር ሳይሆን በተሰጠው ጸጋ ማገልገል ነው። እነዚህ አገልጋዮች በእውነት በፍቅር በእምነት የሚያገለግሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ያመለክታሉ።
፪) የሦስተኛው አገልጋይ ባሕርይ፣ መልካም ጎኑ ስጦታውን አነሰኝ አለማለቱ ነው። በርግጥ ስንፍናውን ስለሚያውቅ ይሆናል። ይህ ሰው ከስራ ይልቅ በስራ ጊዜ የሚፈጠረው ችግር አስቀድሞ ይታየዋል (የሰነፍ አርቆ አስተዋይ) ሲያተርፍ ሳይሆን ሳያተርፍ ብቻ ይታየዋል። አንዱን ሁለት ሲያደርግ ሳይሆን ያንኑ ያለውን ሲቀማ ይታየዋል። በጌታው ፊት እንደወንድሞቹ ዓይነቱን ትርፍ ይዞ ቀርቦ ሲሸለም ሳይሆን ዓይነታውም ጠፍቶበት ለጌታው የሚመልሰውን ሲያጣ ይታየዋል። በመሆኑም ምንም መስራት አልቻለም። የተሰጠውን መክሊት ኪሱን አላምነው ብሎ መሬት ቆፍሮ ቀበረው።
በአጠቃላይ ባለማመን የተያዘ ሰው ነው። ከጌታው ፊትም ሲቀርብ በጎ አገልጋዮቹ ያልተናገሩትን ነው የተናገረው። “ጨቃኝ መሆንህን ስላወቅኩ ይጠፋብኛል ብዬ ብርህን አስቀምጬልሃለሁ፣ ይኽውልህ ና ውሰድ” ነው ያለው። ሰነፍ የሚናገረውም አያምር ተቀምጦም መዓት ከማውራት ዝም አይልም።
ዛሬም ቢሆን ተቀምጠው መዐት የሚያወሩ የእግዚአብሔርን ጸጋ የቀበሩ፣ ባስተምርና መናፍቅ ተከራክሮ ቢረታኝስ ? የማውቀውን እውነት ለመስበክ ስጀምር ቢያሳስሩኝስ ? በቤተ ክርስቲያን በሕዝብ በገበያ በልዩ ልዩ ቦታዎች ያሉትን ኃጢአተኞች ብቃወም ጠላት ሆነው ቢነሱብኝስ ? ለምን ዝም ብዬ ደሞዜን ሳልሰራ አልበላም ብለው የሚኖሩ ስንት አገልጋዮች አሉ። የዚህ ሰው ችግሩ መክሊቱ አንድ መሆኑ ሳይሆን በዚያው በተሰጠው አለመስራቱ ነው። የተሰጠውን ጸጋ እያንዳንዱ አምኖ በመቀበል ሊያገለግል ይገባዋል። ባለ ሁለቱ በባለ አምስቱ፣ ባለ አንዱ በባለ ሁለቱ ሊቀና አይገባውም።
ሁሉም ሊቀ ጳጳስ፣ ጳጳስ፣ ቄስ አይሆንም። ሁሉም ግን በተሰጠው ጸጋ ቢያገለግል እውነተኞች ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት ቀሳውስት የሚያገኙትን ዋጋ ያገኛል። ሁሉም ባለ ራእይ፣ ወንጌላዊ፣ ዘማሪ፣ ፈዋሽ ሊሆን አይችልም። ለእያንዳንዱ ልዩ ጸጋ አለው። ሁሉም በጸጋው ቢያገለግል እኩል ዋጋ ያገኛል።
አንባቢ ሆይ በሶስቱ አገልጋዮች አምሳል የተጠቀሱት አገልጋዮች በቤተ ክርስቲያን የሚኖሩ ልዩ ልዩ የጸጋ አገልግሎት ያላቸው ክርስቲያኖችን የሚመለከቱ ናቸው። በቤተ ክርስቲያን ባለ አምስት አምስት አገልጋዮች አሉ፣ በወንጌል ፣ በእረኝነት፣ በእርዳታ በልዩ ልዩ ጸጋ አንዱን ጌታ በቅንነት የሚያገለግሉ ሰዎች ምሳሌ ናቸው ባለ ሁለቱም እንዲሁ ልዩ ጸጋ ያለው በጸጋውም የሚያገለግል የጌታ አገልጋይ ምሳሌ ነው። ባለ አንዱን ግን ጸጋ እግዚአብሄርን የተቀበለ ግን በጸጋው የማያገለግል ደካማ ሰው ነው። ምናልባትም ይህ ሰው ራሷ ክርስቶስ በሆነላት ቤተ ክርስቲያን እግር ሆኖ ቢፈጠር ኖሮ የማይሄድ፣ እጅ ቢሆን የማይዳሰስ፣ አይንም ቢሆን የማያይ ... ስንኩል አካል ነው። በመሆኑም የክርስቶስ አካል ሆኖ ለመቀጠል አይችልም።