✝አሥሩ_የቅድስና_ማዕርጋት
1 ጽማዌ
2 ልባዌ
3 ጣዕመ ዝማሬ
4 ኩነኔ
5 ፍቅር
6 አንብዓ ንስሐ
7 ሑሰት
8 ተሰጥሞ
9 ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ
10 ከዊነ እሳት ናቸው።
1 ጽማዌ
2 ልባዌ
3 ጣዕመ ዝማሬ፣ ንጽሐ ሥጋ ይባላሉ።
4 ኩነኔ
5 ፍቅር
6 አንብዓ ንስሐ
7 ተሰጥሞ፣ ንጽሐ ነፍስ ይባላሉ።
8 ሑሰት
9 ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ
10 ከዊነ እሳት፣ ንጽሐ ልቡና ይባላሉ።
🥀የሰው ልጅ በዚህ ምድር ሲኖር በቅድስናና በንጽሕና እያደገ ሲመጣ የሚደርስባቸው አሥር መንፈሳዊ ማዕረጋት አሉ፡፡
እነዚህ አሥር መንፈሳዊ ማዕረጋት በሦስት የሚከፈሉ ሲሆን፡- ንጽሐ ሥጋ ፤ ንጽሐ ነፍስና ፤ ንጽሐ ልቡና ይባላሉ፡፡
አሥሩንም ማዕረጋት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
1. #ጽማዌ፡-
ይህ ማዕረግ የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን ትህትናን፤ ራስን ዝቅ ማድረግን፤ መታገሥንና ነገሮችን በውስጥ ይዞ ማሰላሰልን ወዘተ…ይይዛል፡፡
እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው የዚህን ዓለም ውጣ ውረድ ከማውራት ይከለከላል በብዙ ነገሮች ላይ ዝምታን ይመርጣል፡፡
2. #ልባዌ፡-
ይህ ማስተዋልና ልብ ማለትን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች የሚገኙበት ደረጃ ነው፡፡
እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ ሰዎች ልናገር ሳይሆን ልስማ ፤ ላስተምር ሳይሆን ልማር ይላሉ፡፡
የመጽሐፉ ቃል የሚለውን ማስተዋልና አብዝተው ኃጢአታቸውን ያሰላስላሉ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ፡፡
3. #ጣዕመ_ዝማሬ፡-
እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው አንደበቱን ከንባብ ልቡናውን ከምሥጢር ያቆራኛል፡፡
እዚህ ደረጃ የደረሱ ቅዱሳን አንደበታቸው ዝም ቢል በልባቸው ግን ዝም ብለው አያውቁም ከሰውነታቸውም ንጽሕና አይለይም፡፡
የሚያነቡትን መጽሐፍና የሚጸልዩትን ጸሎት ምሥጢሩን በደንብ እየተረዱት ስለሚያደርጉት አይሰለቻቸውም፡፡ እነዚህ ከ1-3 ያሉት የንጽሐ ሥጋ ማዕረጋት ናቸው፡፡
4. #አንብዕ፡-
እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ ሰዎች የጌታቸውን ፍቅር እያሰቡ እስከ ሞትና መከራ የተጓዘውን ጉዞ እያሰቡ ዘወትር ያለቅሳሉ፡፡ ያለምንም ተጽዕኖ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይወርዳል፡፡
ይህንንም የሚያደርጉት ለዚህ ዓለም ፍላጎታቸው መሟላት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ምሕረትና ቸርነት በመናፈቅ ነው፡፡
5. #ኩነኔ፡-
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ሥጋዊ ፈቃድ ሁሉ ለነፍስ ፈቃድ ይገዛል ፤ ነፍስ በሥጋ ፍላጎት ላይ ትሰለጥናለች፡፡ ምድራዊ (ሥጋዊ) ፍላጎቶች ይጠፉና ሰማያዊ (የነፍስ) ፍላጎቶች ቦታውን ይወርሳል፡፡
6. #ፍቅር፡-
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ማንንም ሳይመርጡ ወዳጅንም ጠላትንም መውደድ ይጀምራሉ፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ያደረገውን ታላቁን የፍቅር ሥራ እርሱን በመምሰል ሕይወት በመኖር በተግባር ይገልጻሉ፡፡
7. #ሁሰት፡-
ከዚህ ማዕረግ የደረሱ ቅዱሳን ባሉበት ቦታ ሆነው ሁሉን ነገር ማየት ይችላሉ፡፡ የቦታ ርቀትና የገዘፉ ቁሶች ሳያግዳቸው ፤ ሁሉን ያያሉ፡፡
እነዚህ ከ4-7 ያሉት የንጽሐ ነፍስ ማዕረጋት ናቸው፡፡
8. #ንጻሬ_መላእክት፡-
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ መላእክትን ሲወጡና ሲወርዱ ማየት ይቻላል፡፡
9. #ተሰጥሞ፡-
ከዚህ ማዕረግ የደረሰ ሰው በብርሃን ባሕር እየተመላለሰ በምድሪቱ ላይ ያለውን ሁሉ ማወቅ መረዳትና መመልከት ከመቻላቸውም አልፈው ሥሉስ ቅዱስ ከመመልከት በስተቀር በሰማያት ያለውንም ምሥጢር ወደ መረዳት ይደርሳሉ፡፡
10. #ማዕረገ ከዊነ እሳት/ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ/፡-
ከዚህ ማዕረግ የደረሱ ሰዎች ሥላሴን በዙፋኑ ላይ ሆኖ እንደ እስጢፋኖስ መመልከት ይጀምራሉ፡፡
🥀እንዲሁም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በአካለ ነፍስ ተነጥቀው ወደ ሰማያት በመውጣት ሰማያትን መጎብኘት ወደ መቻል ይደርሳሉ፡፡
🥀የቅዱሳን አምላክ እኛን በቸርነቱ በምህረቱ ለእዚህ የተቀደው ማዕረግ የተመረጥን ያድርገ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯