*የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን*
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሽንት ስርዓት አካላትን ማለትም (ኩላሊትን፣ የሽንት ፊኛን እና የላይኛውን (Ureter) እና የታችኛውን (urethra) የሽንት ማስተላለፊያ ቱቦዎች የሚያጠቃ የኢንፌክሽን አይነት ነው። ብዙዎቹ ኢንፌክሽኖች የታችኛውን የሽንት ቧንቧዎች (Urethra) እና የሽንት ፊኛንና (Urinary Bladder) ያጠቃሉ። ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው። ኢንፌክሽኖች ከሽንት ፊኛ አልፈው ወደ ኩላሊት ከተሻገሩ አሳሳቢ የጤና እክል ሊያስከትሉ ይችላሉ።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድን ናቸው?
አንዳንዴ ምልክት ላያሳይ ይችላል ፤ ካሳዩ ግን ምልክቶቹ እነዚህን ይመስላሉ፣
• በመጠን አነስተኛ ግን በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት
• ደመናማ የመሰለ የሽንት ከለር
• የሽንት ከለር መቀየር – ቀይ፣ ሮዝ ወይም ጠቆር ያለ ሽንት —ከሽንት ጋር የደም ምልክት
• ያልተለመደ ጠንከር ያለ የሽንት ሽታ
• ማህፀን አካባቢ የሚሰማ የመጫን ህመም (ለሴቶች) ወይም ወንዶች ብልታቸው አካባቢ እና የሽንት ፊኛ አካባቢ የሚሰማ ህመም፡፡
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መንሰኤዎች
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ባክቴሪያ ወደ ሽንት ቧንቧ ገብቶ በሚራባበት ጊዜ ነው። የሽንት ስርዓታችን በተፈጥሮ ባክቴሪያዎችን እንዲያስወግድ የተሰራ ቢሆንም አንዳንዴ ተፈጥሮአዊው መከላከያ መንገድ አሰራሩን በማሽነፍ ባክቴሪያዎች ወደ ሰውነታችን ገብተው በሽታ ሊያመጡ ይችላሉ። በተፈጥሮ የብልቶቻችን አቀማመጥ የተነሳ ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የተጋለጡ ናቸው ። የግብረ ስጋ ግንኙነት ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሴቶችን በተለይ የበለጠ ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል።
ሴቶች በተለይ ባላቸው የሰውነት አቀማመጥ (Female anatomy) ምክንያት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት፣ በማህፀን ውስጥ በሚቀመጡ አንዳንድ የወሊድ መከላከያዎች እንዲሁም የሴቶች ማረጥ (Menopause) ጊዜ የበለጠ ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ከፍተኛ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።
ከነዚህም በተጨማሪ የሚከተሉት ሁኔታዎች የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ተጋላጭነትን ይጨምራሉ::
• ጤናማ ያልሆነ የሽንት ቧንቧ ኖሯቸው የሚወለዱ ህጻናት
• የሽንት ቧንቧ መደፈን፦ በኩላሊት ጠጠር ምክንያት
• የበሽታ መከላከያ ስርዓት መጎዳት፦ ለምሳሌ በስኳር በሽታ ምክንያት – ተፈጥሮአዊው በሽታ መከላከያ ብቃት እንዲቀንስ በማድረግ ለኢንፌክሽኑ ተጋላጭ እንድንሆን ያደርጋል።
• አርቴፊሻል የሽንት ቱቦ (ካቴተር )የሚጠቀሙ ህመምተኞች
• የሽንት ፊኛ፣ ፕሮስቴት ወይም የኩላሊት ቀዶ ጥገና ያደረጉ ሰዎች ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የበለጠ ተጋላጭ ናቸው::
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ከበረታ ምን አይነት ችግር ሊያመጣ ይችላል ?
የታችኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን በአግባቡና በጊዜ ከታከመ ለክፉ አይሰጥም። ካልታከመ ግን ከባድ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል። እነዚህም
• ተደጋጋሚ ኢንፌክሽኖች
• ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ኢንፌክሽን እና መዳከም
• ነፍሰጡሮች ላይ ከተከሰተ ደግሞ የሚወለደው ህጻን መጠኑ ከሚገባው ያነሰ ወይም ያለጊዜው ሊወለድ ይችላል።
• Sepsis, ለህይወት አስጊ የሆነ እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል ኢንፌክሽን ነው፤ በተለይ ወደ ኩላሊት የሚዛመት ከሆነ።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መከላከያ መንገዶች ምንድን ናቸው?
1. በቂ ውሃ መጠጣት:- ውሃ መጠጣት ሽንትን ይበርዛል፤ እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንድንሸና በማድረግ ባክቴሪያው ኢንፌክሽን ሳያመጣ ከሽንት ቧንቧ እንዲወርድ ያደርጋል።
2. ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ የሽንት ቧንቧ አካባቢን ማጽዳት፤ እንዲሁም ውሃ በመጠጣት ባክቴሪያው እንዲወገድ ማድረግ፣
3. የሴቶች የተለያዩ የብልት ማጽጃዎች እንደ ዴወደራንት እና ፓውደር አለመጠቀም። እነዚህ አይነት ማፅጃዎች ባክቴሪያ ወደ ሽንት ቧንቧ እንዲገባ እድል ይፈጥራሉ፣
4. የወሊድ መከላከያ መንገዶችን መቀየር ካለብዎት ከሐኪምዎ ጋር ይማከሩ ፣ በተለይ ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚያጠቃዎት ከሆነ። እንደ ዲያፍራም (Diaphragm) ወይም spermicide-treated ኮንደሞች ለባክቴሪያ እድገት አስተዋጽኦ አላቸው።
5. በጊዜ ሐኪምዎን ያማክሩ ፣ መድሃኒት ከታዘዘሎት በአግባቡ ይውሰዱ።