የቦሌ ክ/ከተማ ትናንት ለሊት ብቻ 345 ህገ-ወጥ ቤቶች ተሰርተው አድረዋል ብሏል!
ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ተሰማ አገኘውት ባለው መረጃ መሰረት እነዚህ ቤቶች ለሊቱን ቦሌ ቡልቡላ ወረገኑ አካባቢ በሸራ ተሰርተው ያደሩ መሆናቸውንና ህገ-ወጥ ደላሎች ሂደቱን እየደገፉ መሆኑን ኃላፊው መናገራቸውን ገልጿል።
ከቀናት በፊትም ቦሌ ቡልቡላ አሰር ኮንስትራክሽን ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ተመሳሳይ ድርጊት ተከስቶ እንደነበርና "እኛ በሽታ ለመከላከል ስራ እየሰራንበት ባለበት ወቅት መንግስት ተዘናግቷል ተብሎ የሚደረግ ህገ-ወጥ ስራ ነው" ብለዋል። አቶ ጥላሁን አክለውም "መንግስት እርምጃ እየወሰደ ነው፣ ወደፊትም ይወስዳል" ብለዋል ሲል ጋዜጠኛ ኤልያስ በገጹ ጽፏል፡፡
@dwamharic_news