ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ስለ ክርስትና የምራቸውን ነው?
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በዛሬው የፓርላማ ውሎአቸው እንዲህ አሉ፤
" ... ክርስትና በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ተመሥርቶ የትም ዓለም ሳይስፋፋ የገባው ኢትዮጵያ ነው። ያ ክርስትና ድህነትን ለመምታት "tool" (መሣሪያ ለማለት ይመስለኛል)ኾኖ ማገልገል ነበረበት። ነበረበት ነው አላገለገለም።..." ብለዋል።
በተደጋጋሚ እንዲህ ያለ ተመሳሳይ ወቀሳ፣ ኦርቶዶክስን ከግብጽ ቤተክርስቲያን ጋር አያይዞ ማቅረብ እንግዳ ነገር አይደለም። ይህ የሚሉ ሰዎች እንኳ፣ ሙሉውን የኦርቶዶክስ ክርስትና፣ በደፈናው ሲያጠለሹ አንመለከታቸውም። ከዚህ ዘልሎ ግን በኢትዮጵያ ክርስትና ውስጥ፣ የኢትዮጵያ ክርስትና ጠቅላላው ድህነትን ለመምታት "ያላገለገለ መሣሪያ" ነው ማለት ለእኔ ከባድ ጽርፈት ነው። በሥራ ሕይወታቸውም ኾነ ባህላቸውም አንቱ ተብለው የተከበሩ አገልጋዮችም፤ አማኞችም የነበሩአትና ያላት ርትዕት ክርስትና ዛሬም አለችና!
ይልቁን በክርስትና ስም "ሥራ ፈትና አጭበርባሪ፤ እልል ያሉ ወንበዴ ነቢያትና ሐዋርያት፣ በመንግሥት ስም በተቋቋመ ባንክ ስም ብር የሚያበዛ ATM በጉባኤያቸው ሲያድሉ የሚውሉ፣ ብር አበዛን የሚሉ አለሌ ጌቶችን" በክርስቲያንነት ቆጥረው ከኾነ ልክ አይደለም። እንዲያውም እንዲህ ያሉ "ነቢያትና ሐዋርያት" ከምንጊዜውም በላይ በርሳቸው ዘመን ነውና የበዙት አደብ ቢያሲዙልን መልካም ነው። ቃሉም፦ “ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች ናቸው...፤(ሮሜ 13፥3) ይላልና።
ነገር ግን አንድም ጥናት ባልቀረበበት፣ በደፈናው ክርስትናን እንዲህ ማዋረድ ከአንድ መሪ ፈጽሞ አይጠበቅም። የክርስትና ግልጽ መርህ፣ “ሊሠራ የማይወድ አይብላ”(2ተሰ. 3፥10) ብሎ እንኳን አለመሥራትን፣ ሥራ አለመውደድን የሚጠየፍ ነውና።
የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek