ኢየሱስ ዛሬም በዐውደ ምሕረቱ ይነቀፋል!
"ካራ ኦርቶዶክሳውያን" ኹለንተናዊ በኾነ መንገድ፣ ክርስቶስ እንዳይሰበክና እንዳይዘመር የማይሠሩት ሥራ የለም። ይህን ወንድም በ"ዐውደ ምሕረታቸው" ላይ እንዴት እንደሚያዋክቡት ማየት በቂ ምስክር ነው። ምን እንደምትዘምር እንኳ ይመርጡልሃል፤ በልቤ ያለውን ልዘምር ብትል ልብህን በማዋከብ ያጠፉታል።
የአሸናፊ ገብረ ማርያምን መዝሙር ከዚህ ወከባ በኋላ ሰማኹት፣ መልካም መዝሙር ነው፤ ሳሰላስል ለምን የኢየሱስን ቅሩብነት ጠሉ? አልኹ። የሚፈልጉት የፍጡራንን ቅሩብነት ነው ብዬ ለራሴ መለስኹ፤ በርግጥ እውነታውም ይኸው ነው!
መዝሙሩ እንዲህ ይላል ...
"እንዴት ብለህ ተገኘህ እኔ ቤት
እንዴት አልሰለቸህ መተኛት ከበረት ...
...
እንደ አጭሩ ቀራጭ ሾላ ላይ ብወጣ
ከቤቴ ሊገባ መምህሩ መጣ ...
እናም ... በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የምትሰበከውና በእውነታ ያለችው ኦርቶዶክስ ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ የተለያዩ ናቸው። በሶሻል ሚዲያ ላይ ያለችው "የአንዳንድ ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ኦርቶዶክስ" ተአምራት፣ ገድላት፣ ድርሳናት ... ስህተት አለባቸው ቢሉም፣ እውነታው ግን በቤቱ ውስጥ ለጸሎትና ለአምልኮ ስፍራውን የተቆጣጠሩት እነርሱ ናቸው። በተጨማሪም "ዐውደ ምሕረቱን የተቆጣጠሩት በልብስ ያጌጡ ጨዋዎች፣ ዶግማና ቀኖና የተምታታባቸው፣ ቀኖናን ከዶግማ በላይ የሚያመልኩና ዶግማ ጠል የኾኑ፣ የማኅበረ ቅዱሳን የግብር ልጆች፣ የክርስቶስ ስም ሲጠራ የሚሰላቹ ... ናቸው።
እናም ምዩጣኑ ይህን መዋከብና ኢየሱስ ጠልነትን ኸድደው በመሄዳቸው ያሳዝኑኛል። አዎን ወንጌል በዚያ "ዐውደ ምሕረት ላይ" በትክክል አይፈለግም፤ ደግሜ እላለሁ አይፈለግም። ጌታ ግን ጻድቅና የታመነ ሉዐላዊ ነው።
ወንጌል በምልአት በኦርቶዶክሳውያን መድረክ እስኪሰበክ መትጋትን አንተውም!
የዩቱዩብ አድራሻ -https://youtu.be/_hDd1Qe3q7s?feature=shared