ኦርቶዶክሳውያን መንገድ ቀይረዋልም፤ አልቀየሩምም!
የኦርቶዶክስ ዐቃብያን ወደ ተወሰነ መረዳት የመጡ ይመስላል። ትላንት ለድርሳናት፣ ለገድላት፣ ለተአምራትና ለነገራት ትክክለኝነት፣ ለጸሎትና ለአምልኮ ቢውሉ ችግር የለባቸውም ብሎ የሚሟገቱትን ሙግት ትተዋል ማለት ይቻላል። በርግጥ "ጩሉሌና አልተነቃብንም የሚሉ አንዳንዶቹ"፣ የሙግት ቅኝታቸውን ቀይረው፣ "ገድላትና ድርሳናትን ለሃይማኖት መከራከሪያነት" አልተጠቀምንም ሲሉ እንሰማቸዋለን።
ለሃይማኖት መከራከሪያነት አለመጠቀምን እንደ በጎ ነገር እንዴት ያነሡታል?! ምናልባት አርዮስም ይኹን መቅዶንዮስ ገድል ወይም ተአምር ጠቅሶ ይሞግታል ብለው እንዴት የሞኝነት መከራከሪያ ያነሳሉ?! ከጥንትም የሃይማኖት መከራከሪያ መጽሐፍ ቅዱስ እንጂ ተአምር ወይም ገድል አይደለም፤ ኾኖም አያውቅም።
ገድላት በራሳቸው በኦርቶዶክሳውያን "እስኪታፈርባቸው" ድረስ ዛሬ ላይ በአሉታዊ መንገድ መታየታቸው ይበል የሚያሰኝ ነው። በሚያበረታታ መንገድ ዛሬ ላይ ኦርቶዶክሳውያን በዓውደ ምሕረቶቻቸው የማይደፍሩትን እውነት በማኅበራዊ ሚዲያዎች መናገር ጀምረዋል።
በተቃራኒው ግን ይህን አቋም የያዙ ሰዎች በነዘበነ ለማ እንደ መ-ና-ፍ-ቅ እየተቆጠሩ ነው። እንዲያውም ገድላትንና ተአምራትን "የመጽሐፍ ቅዱስ ያህል ልንቀበላቸው ይገባል" ሲሉ እንሰማዋለን። ዘበነ ለማ ግን ይህን ያህል እንዴት "ይደነዝዛል"? ገድላትና ሌሎች መጻሕፍት ውስጥ ያሉ ነውራትን ሳያውቅ ቀርቶ አይመስለኝም፤ ሰው ግን ካፈርኹ አይመልሰኝ ካለ ልክ እንዲህ እንደ ዘበነ ነው መገለጫው!
የዩቲዩብ አድራሻ -https://youtu.be/UI5rrUV0cxk?feature=shared