የእምነት እንቅሰቃሴ ቀንደኛ አስተማሪው "ፓስተር" ሮን፣ ኢየሱስ "ሰይጥኗል" ባዩና ስለ መለኮታዊ ገንዘብ አቅርቦት አስተማሪው "ሐዋርያ" ዘላለም፣ ሰው መንፈስ ነው ባዩ ጃፒ(ብዙአየሁ) ... እነዚህ ሰዎች "ሐዋርያ" ተብለው ቢጠሩም ሐዋርያት በዋሉበት አልዋሉም፤ አላደሩም፤ አያውቋቸውምም።
እናም የሊሊን ፕሮግራም አድማቂዎች እኒህ ነበሩ። ቅዱስ ጳውሎስ፣ "ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ እኔ ራሴ ውድቅ ሆኜ እንዳልቀር፣ ሰውነቴን እየጐሰምሁ እንዲገዛልኝ አደርገዋለሁ።" (1ቆሮ. 9፥27 ዐመት) እንዲል፣ ሊሊን፤ አገልግሎ መጣል፤ ጥሩ ዘምሮና ሰብኮ በጌታ ፊት ውድቅ መኾን እንዳለ ይህን የጳውሎስ ምክር ማን በመከራት እላለኹ?!
መጽሐፍ በጥልቅ ምክሩ እንዲህ ይላል፣ "አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።” ወደ ሰከነ ልቦናችሁ ተመለሱ፤ ኀጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና፤ ይህንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው።" (1ቆሮ. 15፥33-34) ይላል። ሊሊንም እንዲህ፣ አንቺ የዘመርሽለትን ጌታ ከማያውቁ ጋር ምን በአምልኮና በ"ዐውደ ምሕረት" አጎራበተሽ?! ...
ኢየሱስ ሰሚ ባጣ ጊዜ እንደ ተናገረው እላለኹ፣ "የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ"። ከአጀብ ተነጠሉ ከኢየሱሰ ጋር ተስማሙ፤ ከሐሰተኞች መንጋ ሽሹ፣ ኢየሱስ ከሚከብርበት ኹለትም ሰዎች ካሉበት ኅብረት ተጣበቁ፤ አትሳቱ፤ የክብር አምላክ በሰማያት በዙፋኑ አለ፤ ርሱ በጽድቅ እርሻ ውስጥ የተዘራውን እንክርዳድ ኹሉ ሳይቀር፣ ሲለቅምና ሲለይ አይሳሳትም፤ ፍጹም ጻድቅ ነውና!
ለገንዘብና ለክብር ብላችኹ ዕንቁ እምነታችሁን በዕሪያ ፊት አታስረግጡ።
የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek