“በዚህ ህይወት ውስጥ መገናኘትም ሆነ መለያየት ተፈጥሯዊ የህይወት ህግጋት ናቸው። ከሰዎች ጋር በምንኖረው የዕለት ተዕለት ግንኙነት፣ በትዳርም ሆነ በስራ፣ በጓደኝነትም ሆነ በቤተሰብ ደረጃ ሁልጊዜ ነገሮች እንደጠበቅናቸው ብቻ ላይሄዱ ይችላሉ። ሆኖም ግን አንድ ትልቅና የሰለጠነ ስብዕና ያለው ሰው የሚለካው በግንኙነቱ መጀመሪያ ላይ በሚያሳየው ደግነት ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎችን በሚለያይበትና በሚጣላበት ወቅት በሚያሳየው ስነ-ምግባርና ክብሩ ነው።