ᏃᗩᏦᏆᖇ’Official Channel”


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Books


ትክክለኛውን የኢስላም እምነት (አቂዳ) እና የነብዩን ﷺ ሱና በሰለፎች (ቀደምት ደጋግ አባቶች) ግንዛቤ የምናሰራጭበት ቻናል ነው።

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Books
Statistics
Posts filter



1.4k 0 2 150 143

“ሰው እንዴት ሳምንት ሙሉ ስለ ሰው ያወራል?
እባካችሁ አላህን እንፍራ! ቀብር የሚባል የማይቀር እውነት አለ እኮ።
….ሰው የራሱ ህይወት፣ የራሱ ትግል አጥቶ ነው የሌላውን ህይወት ተሸክሞ ሳምንት ሙሉ ሲያኝክ የሚውለው? የሰው ስጋ ከመብላት የራሳችንን ህይወት ብናስተካክል አይሻልም?"

አረ ተቃጠልን እኮ ወገን

1.4k 0 0 23 118

“በአንድ በኩል፦ «ገንዘብህን ቆጥብ፤ ወደፊት ያስፈልግሃል!» የሚልህ አእምሮ…

በሌላ በኩል፦ «ኧረ አንድ ሺ! ዓመት አትኖርም፤ ፏ በልበት!» የሚልህ አእምሮ…

እነዚህ ሁለቱ ሰላም ካላወረዱ፣ ሀብታም መሆን ህልም ሆኖ ይቀራል! 😂💸

1.6k 0 3 53 160

ቀናት ይሄዳሉ፤ አይቆሙም። እኛም ሳናስበው ከአንድ ቀን ወደ ሌላ እየተሻገርን ነው። ሕይወትም በኪሷ ብዙ ነገሮችን ይዛ ትጓዛለች፤ አንዱ መልካም፣ ሌላው መጥፎ ሊሆን ይችላል።

አንዳንዴ ከጤና እስከ ሀብት ማጣት፣ ከደስታ እስከ ሀዘን፣ ከስኬት እስከ ፈተና ድረስ በፍጹም ያላሰብነው ነገር ሊገጥመን ይችላል። ስለዚህ ለደጉም ሆነ ለክፉው በሥነ-ልቦና መዘጋጀት ግድ ይለናል። ዛሬ ያለንበት ሁኔታ ሁሌም እንደሚቀጥል ማሰብ የለብንም፤ ሕይወት ተለዋዋጭ ናት።
ከሁሉም በላይ ግን ኢማናችንን እንዳንከስር እንጠንቀቅ። ከኢማን በስተቀር የምናጣው ኪሳራ ሁሉ በአንፃራዊነት ትንሽ ነው። ሀብት ሊመለስ ይችላል፣ ጤናም ሊታደስ ይችላል፣ የጠፋ ነገርም በሌላ ሊተካ ይችላል፤ ነገር ግን ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ማጣት ከሁሉም ትልቁ ኪሳራ ነው።

ᏃᗩᏦᏆᖇ’Official Channel”

1.7k 0 2 33 151

አንዴ ቀስ ብላቹ ተጠጋጉ እስኪ!!😎

2.1k 0 0 40 104

«ደህና እደሩ! ህልማችሁ ሁሉ በቡና መዓዛ የተሞላ ይሁን!»

وسلام عليكم ورحمة الله وبركاته

2.2k 0 2 70 166

"ሲከፋህ መኖርህ ትርጉም ያጣ ይመስልሀል፤ ነገር ግን ያንተ በህይወት መኖር እንደ አየር የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ፤ ባዶነትና ድካም የሁሉም ሰው የጉዞ አካል ነው፤ ወሳኙ ነገር ግን በዛች ጨለማ ቅፅበት እንኳን፣ ያንተ ወደዚህ አለም መምጣት ህይወታቸው ላይ ትልቅ ሀይልና ተስፋ የሚጨምርላቸው አያሌ ሰዎች መኖራቸውን ማሰብ ነው።

በሉ ፈየ እንደሩ!!

2.6k 0 14 58 179

ሲጀመር ላጤና ቡና የማይጠጣ ሰው ሁለቱም አንድ ናቸው፤ ቶሎ ነው “ብሶት ብሶት” የሚላቸው! ወይ አግቡ ወይ ቡና ጠጡ! 😂☕️

4.6k 0 30 72 161

ትክክለኛ ደዕዋ ወደ ላ ኢላሃ ኢለላህ መጣራት ነው


“ትክክለኛ ደዕዋ ማለት ሰዎችን ወደ አላህ ብቻ መጣራት፣ የተውሒድን እውነት ማብራራት እና “ላ ኢላሃ ኢለላህ” የሚለውን ቃል በትክክለኛ ትርጉሙና በሚገባው መልኩ ለሰዎች ማስተማር ነው። ደዕዋ ዓላማው ሰዎችን ወደ ፈጣሪያቸው ማቅረብ እንጂ የራስን ስም ማሳደግ ወይም ሌሎችን ማዋረድ አይደለም።

ነገር ግን ዛሬ ነገሩ መልኩን ቀይሮ የምናየው ነገር አለ። ወደ ላ ኢላሃ ኢለላህ የሚጣሩ፣ ተውሒድን የሚያስተምሩ ወንድሞችን ማጥላላት፣ ማዋረድ፣ ስማቸውን ማጥፋትና ሰዎችን ከእነሱ ማራቅ እንደ ደዕዋ ወይም እንደ መንሀጅ የሚታይበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው። ይህም ደዕዋ ወደ ምን እንደተለወጠ በጥልቀት እንድንጠይቅ ያስገድደናል።

ወንድማችን ላ ኢላሃ ኢለላህን እየጣራ ከሆነ፣ የተውሒድን አስፈላጊነት እያስተማረ ከሆነ፣ የሽርክን አደገኛነት እያስጠነቀቀ ከሆነ፣ ልዩነት ቢኖረን እንኳን በማስረጃና በፍትሕ መወያየት ነው የሚገባው፤ ማጥላላትና ማዋረድ ግን የደዕዋ ዓላማ ሊሆን አይገባም።

የደዕዋ ሰው ራሱንም ጭምር መፈተሽ አለበት። “ሰዎችን ወደ አላህ እየጣራሁ ነው? ወይስ ሰዎችን ወደ ራሴና ወደ ቡድኔ እየጣራሁ ነው?” ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። እውነተኛ ደዕዋ ሰውን ወደ አላህ ታስጠጋለች፤ ልብን በእውቀት፣ በተውሒድ፣ በኢኽላስ ታሳድጋለች።

ስለዚህ ዛሬ የሚያስፈልገን የሌላውን ስም ማውረድ ሳይሆን ወደ አላህ መመለስ፣ የተውሒድን እውቀት ማስፋፋት፣ በቁርኣንና በሱንና ላይ በማስረጃ መናገር እና በመካከላችን ፍትሕንና መልካም ምክርን ማስፈን ነው።

ደዕዋ ወደ አላህ እንጂ ወደ ሰው አይደለም፤ የደዕዋ መለኪያም ሰዎችን ማዋረድ ሳይሆን ሰዎችን ወደ ተውሒድና ወደ አላህ ታዛዥነት መጣራት ነው።

ᏃᗩᏦᏆᖇ’Official Channel”

2.2k 0 1 27 127

“እሺ አንዴ ሰብሰብ በሉ”😁


“ዛሬ በኡማችን ዘንድ እጅግ የሚያስዝነው ነገር ቢኖር፣ የተቀደሰውን የሐዲሥ ሳይንስ ሚዛን (ጀርህ ወተዕዲልን) ዓላማውን በሳተ መልኩ በመጠቀም የወንድማማችነትን ገመድ የሚበጥሱ ድርጊቶች መብዛታቸው ነው። ወንድሞችን ያለ በቂና ህጋዊ የሸሪዓ ማስረጃ ከሱና እና ከሰለፊያ መስመር ማስወጣት የተለመደ ተራ ነገር ሆኗል።
ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ፣ ዕድሜያቸውን ሙሉ በዒልም፣ በዳዕዋ እና በሱና አገልግሎት ያሳለፉትን እንደ ሼክ ኤሊያስ አህመድ ያሉ ታላላቅ የዲን መምህራንን እንኳን ሳይቀር «ኢኽዋን ናቸው» እያሉ ስም ለማጥፋት መሞከራቸው ነው። ይህ የሚያሳየው መመዘኛው የሸሪዓ እውቀት ሳይሆን፣ አላስፈላጊ የትዕቢትና የስሜተኝነት አካሄድ መሆኑን ነው።
እኛ አላህን በመፍራትና ሀያእ በማድረግ አንደበታችንን ሰብስበን እንጂ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ Live እየከፈቱ ሰዎችን መሳደብ እና ስም ማጥፋት እጅግ ቀላሉ ነገር ነበር። ነገር ግን አላህ ዘንድ በቃልና በተግባራችን እንደምንጠየቅ ስለምናውቅ አንደበታችንን እንጠብቃለን።
ከሁሉም በላይ የሚያዝነውና የሚገርመው ግን እነዚህ ስም አጥፊዎች ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም በእነሱ ስብስብ ውስጥ ቁጭ ብለው፣ ሌሊትና ቀን በንፅፅርና በዳዕዋ የሚደክሙ እንዲሁም የኡማውን ህመም የሚያክሙ ወንድሞች ሲሰደቡና ሲንቋሸሹ በዝምታ የሚያዳምጡት ወንድሞችና እህቶች ናቸው። በበጎ ሥራ ላይ ካሉ ወንድሞች ጎን መቆም ሲገባ፣ የስም ማጥፋት መድረክ አዳማጭ መሆን ትልቅ የልብ በሽታ ነው።
አላህ ለሁላችንም ቀጥተኛውን መንገድ ያሳየን፤ ልቦናችንንም ያራራልን።

ᏃᗩᏦᏆᖇ˙Official Channel

2.4k 0 1 32 100


2.2k 0 1 24 139

“ለላጤዎች የሚሇን አዲስ ግጥም ልገጥም ነው አበረታቱኝ”።

2.4k 0 3 183 317

አላቹ ግን?🤔

2.4k 0 0 76 111

ቀዳ እና ቀደር (القضاء والقدر)


1. ቀዳእና ቀደር ምንድነው?

ቀደር (القدر) ማለት አላህ ﷻ ነገሮችን ከመፍጠሩ በፊት በዕውቀቱ ማወቁ፣ መመዘኑና መወሰኑ ነው።

ቀዳእ (القضاء) ደግሞ አላህ የወሰነው ነገር በጊዜው መከሰቱና እውን መሆኑን ይጠቃልላል። ከዑለማዎች መካከል በእነዚህ ሁለት ቃላት ትርጉም ላይ የተለያዩ ዝርዝር ገለጻዎች አሉ፤ ነገር ግን ዋናው እምነት አላህ የሁሉንም ነገር ዕውቀትና ውሳኔ አለው፣ የሚሆነውም በእርሱ ፈቃድ ነው የሚለው ነው።

2. ቀዳ እና ቀደር የኢማን አካል ነው

ጂብሪል عليه السلام ወደ ነቢዩ ﷺ መጥቶ ስለ ኢማን ሲጠይቅ፣ ነቢዩ ﷺ ከኢማን አካላት መካከል፦

«وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ»

“በቀደር፣ በመልካሙም ሆነ በመጥፎው፣ ማመን” መሆኑን ገለጹ።
(ሰሒሕ ሙስሊም)

ስለዚህ ቀደርን መካድ ወይም “አላህ አያውቅም፣ ነገሮች ያለ እርሱ ውሳኔ ይከሰታሉ” ማለት የኢስላማዊ እምነትን መሠረት ይጎዳል።

3. ቀደር አራት ደረጃዎች አሉት

የአህሉስ-ሱና ዑለማዎች ቀደርን በአራት ዋና ደረጃዎች ያብራራሉ፦

① አል-ዒልም — የአላህ ዕውቀት

አላህ ﷻ ያለፈውን፣ ያለውንና ወደፊት የሚሆነውን ሁሉ ያውቃል።

አላህ እንዲህ ይላል፦

﴿وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ﴾

“አላህ በሁሉም ነገር ዐዋቂ ነው።”
(አል-በቀራህ 2፥282)

② አል-ኪታባህ — መጻፍ

አላህ ﷻ የሚሆነውን በላውሕ አል-መሕፉዝ ጽፎታል።

አላህ ﷻ እንዲህ ይላል፦

﴿مَا أَصَابَ مِنْ مُصِيبَةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي أَنْفُسِكُمْ إِلَّا فِي كِتَابٍ مِنْ قَبْلِ أَنْ نَبْرَأَهَا﴾

“በምድርም ሆነ በራሳችሁ ላይ የሚደርስ አደጋ እኛ ከመፍጠራችን በፊት በመጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ነው።”
(አል-ሐዲድ 57፥22)

③ አል-መሺኣህ — የአላህ ፈቃድ

በዓለም ውስጥ የሚከሰት ሁሉ ከአላህ ፈቃድ ውጭ አይሆንም።

﴿وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ﴾

“እናንተ አትሻም አላህ ካልሻ በስተቀር።”
(አል-ኢንሳን 76፥30)

④ አል-ከልቅ — መፍጠር

አላህ ﷻ የሁሉም ፈጣሪ ነው።

﴿اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ﴾

“አላህ የሁሉም ነገር ፈጣሪ ነው።”
(አዝ-ዙመር 39፥62)



4. ይህ ማለት ሰው ምርጫ የለውም ማለት ነው?

አይደለም።

ይህ በቀደር ጉዳይ በጣም አስፈላጊ ነጥብ ነው። ኢስላም ሰው ምንም ምርጫ የሌለው እንደ ተገደደ ነገር አያስተምርም።

ሰው መልካምን ወይም መጥፎን ለመምረጥ ፈቃድና ችሎታ አለው። ስለዚህ ለምርጫው ይጠየቃል።

ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ሰላት ለመስገድ ቆመ። ይህን በግድ አልተደረገም፤ እርሱ ፈልጎና መርጦ ነው የሚሰግደው። ሌላ ሰው ሌብነትን ከመረጠም በራሱ ምርጫ ነው።

ነገር ግን የሰው ፈቃድ ከአላህ ፈቃድ ውጭ አይደለም።



5. “ቀደር እንዲህ ነው” ብሎ ኃጢአትን ማመካኘት ይቻላል?

አይቻልም።

ሰው ኃጢአት ሲሠራ “አላህ እንዲህ ጽፎልኛል፤ ስለዚህ ኃጢአቱ የእኔ ጥፋት አይደለም” ማለት ትክክል አይደለም።

አላህ ለባሮቹ መልካምን አዝዟል፣ ክፉንም ከልክሏል። ሰው ደግሞ የሚሠራውን ይመርጣል።

ስለዚህ፦

ከኃጢአት በፊት → ትእዛዝን መከተልና ከኃጢአት መራቅ አለብህ።

ኃጢአት ከተፈጸመ በኋላ → ተውበት ማድረግ አለብህ፤ “ቀደር ነው” ብለህ ራስህን አትመካከር።



6. በሰው ላይ የሚደርስ መከራ ሲኖር ቀደርን ማመን

አንድ ሰው ሀብቱን አጣ፣ በሽታ ደረሰበት፣ የሚወደውን ሰው አጣ፣ ወይም ሌላ መከራ ደረሰበት ከሆነ እንዲህ ብሎ ማመን አለበት፦

“ይህ በአላህ ዕውቀትና ፈቃድ ነው፤ አላህም በዚህ ውስጥ የማላውቀው ጥበብ አለው።”

አላህ ﷻ እንዲህ ይላል፦

﴿مَا أَصَابَ مِنْ مُصِيبَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ وَمَنْ يُؤْمِنْ بِاللَّهِ يَهْدِ قَلْبَهُ﴾

“ምንም መከራ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በቀር አይደርስም፤ በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን ይመራለታል።”
(አት-ተጋቡን 64፥11)

ይህ ማለት ሙስሊሙ መከራ ሲመጣ እጁን አጣጥፎ እንዲቀመጥ አይደለም። መከራን ለማስወገድ የሚችለውን ምክንያት ይወስዳል፣ ከዚያም በአላህ ይመካል።



7. ቀደር ማመን ማለት ምክንያቶችን መተው አይደለም

አንድ ሰው፦ “ሁሉም በቀደር ከሆነ ለምን እሠራለሁ?” ቢል መልሱ፦ አላህ የውጤቱን ብቻ ሳይሆን ምክንያቶቹንም ወስኗል።

ስለዚህ ለምሳሌ፦

ረሃብ → ምግብ ትፈልጋለህ።
ጥማት → ውሃ ትጠጣለህ።
ህመም → ሕክምና ትፈልጋለህ።
ድህነት → ለመስራት ትጥራለህ።
የአኺራ ስኬት → ኢባዳ፣ ተውበትና መልካም ሥራ ታደርጋለህ።

ተወኩል (በአላህ መመካት) ማለት ምክንያትን መተው ሳይሆን ምክንያቱን ወስደህ ውጤቱን በአላህ ላይ መተው ነው።

8. ቀደር ምስጢር ነው

እኛ ቀደርን እናምናለን፤ ግን የቀደርን ሙሉ ምስጢር ማወቅ አንችልም።

ስለዚህ “ለምን አላህ ይህን እንዲሆን ፈቀደ?” የሚለውን ሁሉ ማወቅ አንችልም። አላህ ግን ጥበበኛ ነው።

﴿وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ﴾

“አላህ ዐዋቂና ጥበበኛ ነው።”



9. ቀደር በሙስሊም ሕይወት የሚያመጣው

ቀደርን በትክክል የሚያምን ሰው፦

መልካም ነገር ሲያገኝ → አይኮራም፣ አላህን ያመሰግናል።

መከራ ሲደርስ → ተስፋ አይቆርጥም፣ ይታገሳል።

ነገር ሲያመልጠው → “ቢሆን ኖሮ…” ብሎ ራሱን አያሰቃይም።

ኃጢአት ሲሠራ → ቀደርን ሰበብ አያደርግም፣ ወደ አላህ ይመለሳል።

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

“በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጠንክር፣ ከአላህ እርዳታን ፈልግ፣ አትደክም። አንድ ነገር ቢደርስብህ ‘ባደርግ ኖሮ እንዲህ ይሆን ነበር’ አትበል፤ ‘ይህ የአላህ ቀደር ነው፣ የፈለገውን ያደርጋል’ በል።”
(ሰሒሕ ሙስሊም)

10. በአጭሩ የቀደር እምነት

ቀደርን ማመን ማለት፦

አላህ ሁሉን ያውቃል፤ ሁሉን ጽፏል፤ ሁሉ በእርሱ ፈቃድ ይከሰታል፤ አላህም የሁሉም ፈጣሪ ነው። በተመሳሳይ ጊዜ ሰው ፈቃድና ምርጫ አለው፣ በምርጫውም ይጠየቃል።

ስለዚህ ሙስሊሙ ከመሞከር በፊት “ቀደር ነው” አይልም፤ ከሞከረ በኋላ ውጤቱ እንዳሰበው ካልሆነ “ይህ የአላህ ቀደር ነው” ብሎ ልቡን ያረጋጋል።

ይህ ነው በቀደር ማመን፦ ምክንያትን መውሰድ + አላህን መተማመን + በውጤቱ መታገስ + በችሮታው ማመስገን።

ᏃᗩᏦᏆᖇ˙Official Channel”

2.8k 0 34 19 127

“ስለ ቀደር (የአላህ ውሳኔ) አሪፍ ጽሑፍ ልለቅላችሁ ነው፤ ተዘጋጁ✨

2.5k 0 2 26 128

Video is unavailable for watching
Show in Telegram
“የዚህን ወንድም ስም ጠርቼ ላለመናገር በጣም አስቤበት ነበር። ነገር ግን ይህ ልጅ ወንድሞችን መሳደብ እና ማጥላላትን እንደ መደበኛ ሥራው አድርጎ ይዞታል። አላህ ሂዳያ ይስጠው! ነገር ግን እኔን የሚገርሙኝ እሱ ጋ ቁጭ ብላችሁ ወንድሞቻችሁ ሲብጠለጠሉ የምታዳምጡ እህቶች ናቸው፤ አላህን ፍሩ፣ እሱ ቤት አትቀመጡ!

2.8k 0 16 134 158

“በዚህ ህይወት ውስጥ መገናኘትም ሆነ መለያየት ተፈጥሯዊ የህይወት ህግጋት ናቸው። ከሰዎች ጋር በምንኖረው የዕለት ተዕለት ግንኙነት፣ በትዳርም ሆነ በስራ፣ በጓደኝነትም ሆነ በቤተሰብ ደረጃ ሁልጊዜ ነገሮች እንደጠበቅናቸው ብቻ ላይሄዱ ይችላሉ። ሆኖም ግን አንድ ትልቅና የሰለጠነ ስብዕና ያለው ሰው የሚለካው በግንኙነቱ መጀመሪያ ላይ በሚያሳየው ደግነት ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎችን በሚለያይበትና በሚጣላበት ወቅት በሚያሳየው ስነ-ምግባርና ክብሩ ነው።

2.9k 0 7 19 161

"የነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) መውሊድ መከበር የጀመረው እሳቸው ካለፉ ከ600 ዓመታት በኋላ ነው። ከእሳቸውም ሆነ ከሶሃቦች በኋላ በበጎ መንገድ የተከተሏቸው ትውልዶች (ሰለፎች) ያላደረጉትና ያልደነገጉት አዲስ ነገር እንዴት የሃይማኖቱ (የዲኑ) አካል ሊሆን ይችላል?" ጎበዝ🤔

2.6k 0 2 32 154

"አህባቢ... በአሁኑ ወቅት እጅግ የሚገርም ማህበራዊ ውልቀትን ታዘብኩ። ሰው ደስታውንም ሆነ ሀዘኑን በልቡ ከማኖር ይልቅ ስክሪን ላይ 'እስቶሪ' በማድረግ ተጠምዷል።
ቁጭ ብሎ በግንባር ከመነጋገር፣ ችግርን ተጋርቶ ከማቃለል እና እጅን ወደ ላይ ዘርግቶ ዱዓ ከመድረግ ይልቅ—በቪዲዮና በፎቶ እስቶሪ 'ሀዘኔን/ደስታዬን እዩልኝ' ማለት ቀሎናል። ተበርቼ ሰላም።

2.8k 0 7 80 202
20 last posts shown.