“ዛሬ በኡማችን ዘንድ እጅግ የሚያስዝነው ነገር ቢኖር፣ የተቀደሰውን የሐዲሥ ሳይንስ ሚዛን (ጀርህ ወተዕዲልን) ዓላማውን በሳተ መልኩ በመጠቀም የወንድማማችነትን ገመድ የሚበጥሱ ድርጊቶች መብዛታቸው ነው። ወንድሞችን ያለ በቂና ህጋዊ የሸሪዓ ማስረጃ ከሱና እና ከሰለፊያ መስመር ማስወጣት የተለመደ ተራ ነገር ሆኗል።
ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ፣ ዕድሜያቸውን ሙሉ በዒልም፣ በዳዕዋ እና በሱና አገልግሎት ያሳለፉትን እንደ ሼክ ኤሊያስ አህመድ ያሉ ታላላቅ የዲን መምህራንን እንኳን ሳይቀር «ኢኽዋን ናቸው» እያሉ ስም ለማጥፋት መሞከራቸው ነው። ይህ የሚያሳየው መመዘኛው የሸሪዓ እውቀት ሳይሆን፣ አላስፈላጊ የትዕቢትና የስሜተኝነት አካሄድ መሆኑን ነው።
እኛ አላህን በመፍራትና ሀያእ በማድረግ አንደበታችንን ሰብስበን እንጂ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ Live እየከፈቱ ሰዎችን መሳደብ እና ስም ማጥፋት እጅግ ቀላሉ ነገር ነበር። ነገር ግን አላህ ዘንድ በቃልና በተግባራችን እንደምንጠየቅ ስለምናውቅ አንደበታችንን እንጠብቃለን።
ከሁሉም በላይ የሚያዝነውና የሚገርመው ግን እነዚህ ስም አጥፊዎች ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም በእነሱ ስብስብ ውስጥ ቁጭ ብለው፣ ሌሊትና ቀን በንፅፅርና በዳዕዋ የሚደክሙ እንዲሁም የኡማውን ህመም የሚያክሙ ወንድሞች ሲሰደቡና ሲንቋሸሹ በዝምታ የሚያዳምጡት ወንድሞችና እህቶች ናቸው። በበጎ ሥራ ላይ ካሉ ወንድሞች ጎን መቆም ሲገባ፣ የስም ማጥፋት መድረክ አዳማጭ መሆን ትልቅ የልብ በሽታ ነው።
አላህ ለሁላችንም ቀጥተኛውን መንገድ ያሳየን፤ ልቦናችንንም ያራራልን።

ᏃᗩᏦᏆᖇ˙Official Channel