አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ ዲጂታል የተባለ የትምህርት ቤት የክፍያ አገልግሎትን በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።
አገልግሎቱ በተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ወይም ወላጆችን የትምህርት ቤት ክፍያዎችን ወደ ተቋማቶቹ መሄድ ሳያስፈልጋቸው ካሉበት ሥፍራ በበይነ መረብ አማካኝነት በቀላሉ መክፈል የሚያስችል ዘመናዊ ስርዓት ነው።
ይህው ዛሬ ይፋ የሆነው የአዲስ ኢንተርናሽናል አዲስ ዲጂታል የት/ቤት የክፍያ ስርዓት የትምህርት ቤት ክፍያን በጥሬ ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚጠፋውን አላስፈላጊ ጊዜና ድካም በማስቀረት ቀላልና አስተማማኝ ዲጂታል የት/ቤት ክፍያ አሰራርን ለመዘርጋት የሚያስችል ነው ተብሏል።
ባንኩ ጊዜ ቆጣቢ፣ አመቺና ችግር ፈቺ የሆነ ዘመናዊ የዲጂታል አማራጮችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ በማስጀመሪያ መርኃግብሩ ላይ ተገልጿል።
ብሩክ አስቀናው ያደረሰን ዘገባ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews