የኢቢኤስ አዲስ ነገር በዛሬ የቅዳሜ እኩለ ቀን የትኩረት ጥንቅሩ ተከታዩን ጉዳዪች ይዞ ይጠብቃችኋል፡_
📺ትጥቅ ትግልን በመተው በቅርቡ ወደሰላም የመጡ የሸኔ ታጣቂዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል የምክክር ሂደት እንዲገቡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለጣቢያችን ስለማስታወቁ፤
📺መንግስት የውጪ ባንኮች ወደ አገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቅደውን አዋጅ ቢያጸድቅም አንዳንድ የአገር ውስጥ ባንኮች ሂደቱ ሊያስከትል የሚችለውን ጫና ለመቋቋምና ሊያስገኝ የሚችለውን እድል ለመጠቀም እራሳቸውን እያዘጋጁ አይደለም ስለመባሉ፤
📺ከ2017 መስከረም ወር ጀምሮ ለቀጣይ አራት አመታት ተግባራዊ የተደረገው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ቀደም ብሎ የተደረገ በመሆኑ ድጋሚ ሊከለስ ይገባል ስለመባሉ፤
📺ከአገር ቤት መረጃችን ስንወጣ ደግሞ አለም እንዴት ሰነበተች ስንል ወደ ሶሪያ በወፍ በረር አቅንተን የበሽር አላሳድ መንግስት መውደቅን ተከትሎ እስራኤል በሶሪያ ላይ መጠኑ የበዛ ጥቃት እየፈጸመች ነው ስለመባሉ፤
📺የቅዳሜ የትኩረት ዝግጅታችንን የምንቋጨው የሳምንቱ አዳዲስ የመዝናኛው ዓለም መረጃዎችን ከአገር ውስጥና ከባህር ማዶ የምናቀርብላችሁ ይሆናል ክቡራን ተከታታዮቻችን፡፡
የእኩለ ቀን 7:00 ሰዓት ቀጠሮአችሁን ከቅዳሜ የትኩረት ዜናዎቻችን ጋር እንድታደርጉ ከወዲሁ እየጋበዝን ባልደረቦቻችን እስክንድር ላቀው እና ሳምሶን በላይ እናንተን የሚጠብቁ ይሆናል፡፡
ከወዲሁ ያማረ ቅዳሜ ተመኘን!
"ዜና አዲስ ነገር ነው! አዲስ ነገርም ዜና ነው"