❇️11ኛው አገር አቀፍ ኢግዚቢሽንና ባዛር ከመጪው ጥር 28 እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን አስታውቋል።
❇️በኢግዚብሽኑ ከ350 በላይ አምራችና ሸማች የህብረት ስራ ማህበራትና ከ100 በላይ ልማታዊ ድርጅቶች ይሳተፉበታል ተብሏል።
❇️በተጨማሪም የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶችን ጨምሮ የተለያዩ ምርቶች እንደሚቀርቡ የተገለፀ ሲሆን፣ከአዲስ አበባ ብቻ ከ120 በላይ የህብረት ስራ ማህበራት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተነግሯል።
❇️ከአዲስ አበባ ብቻ 110 የምርት አይነቶች ዝግጁ እንደተደርጉ የተነገረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለሸማች የሚቀርብ 20ሺ ኩንታል የግብርና ምርት ይገኝበታል ነው የተባለው።
❇️ከአዲስ አበባ በተጨማሪ የተለያዩ ክልሎች ምርታቸውን የሚያስተዋውቁበት ቦታ በነፃ እንደተሰጣቸው የተገለፀ ሲሆን፣በመርሃግብሩም የፓናል ውይይት እንዲሁም በዘላቂነት የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚረዱ የልምድ ልውውጦች እንደሚደረጉ ተመልክቷል።
መረጃውን ያደረሰን ሪፓርተራችን ደስዬ ልባይ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews