በአንድ ጊዜ እስከ 10ሺህ ሰዎችን እንደሚያስተናግድ የተነገረለት የአዲስ አበባ ኮንቬንሽ ማእከል በትላንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተመርቆ ተከፍቷል።
ይህ 40 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈና 10 የህንፃ ብሎኮችን የያዘ ማእከል ከህንፃዎቹ ውጪ ባለው ቦታ እስከ 50 ሺህ ሰው መስሰብ የሚችል የኤግዚቢሽን ቦታንም ጭምር መያዙ ነው የተነገረው።
ይህን ግዙፍ ማእከል ባማረ መልኩ ጨረስነው እንጂ እኛ አልጀመርነውም ሲሉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከረጅም አመታት በኋላ ትኩረት አግኝቶ እንዲጠናቀቅ የተደረገው ወዳልጠቀሱት አንድ አገር ተጉዘው ተመሳሳይ ማእከልን ከጎበኙ በኋላ መሆኑን ጠቅሰዋል።
8 መካከለኛና 2 ትልልቅ የስብሰባ አዳራሾችን ይዟል የተባለው ማዕከሉ ባለ 5 ኮከብ ዘመናዊ ሆቴልን ጨምሮ 2 የገበያ ማእከላትና አንፊ ቴአትር እንዲሁም የውሀ ፓርክን ያካተተ ነው ተብሏል።
በአንድ ጊዜ እስከ 2ሺ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው የተነገረለት ይህ ማዕከል በቀጥታ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የሚያገናኘው የመንገድ መሰረተ ልማት እየተዘረጋለት መሆኑም ተጠቁሟል።
በዚሁ ጊዜም የዚህ ማእከል 96 በመቶ ድርሸ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለቤትነት ስር እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን ቀሪው 4 በመቶ በፌዴራል መንግስት የልማት ድርጅቶች ና በግሉ ዘርፍ የተያዘ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
ዘገባው የአቤል አበበ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews