👉አገልግሎቱ ለጊዜው በሀያት፣ ጦርሀይሎች፣ ዳግማዊ ሚኒሊክና ቃሊቲ ጣቢያዎች እንዲሁም በስታዲየም እንደሚጀመር ነው የተነገረው።
👉የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ባለፉት 10 ዓመታት በ39 የትኬት መቁረጫ ጣቢያዎች የወረቀት ትኬት በመሸጥ የቀላል ባቡሩ አገልግሎቱን ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሶ አሁን ግን ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂ በመጠቀም ደንበኞች ካሉበት ሆነው ትኬቱን መቁረጥ የሚችሉበትን አሰራር መዘርጋቱን አሳውቋል።
👉የክፍያ ሥርዓቱ በቴሌ ሱፐር አፕና በሌሎች የክፍያ መተገበሪያዎች አማካኝነት መቁረጥ እንደሚቻል ሲገለፅ ይህም ደንበኞች የትኛውንም አይነት ስልክ በመጠቀም አገልግሎቱን ማግኘት የሚያስችላቸው ነው የተባለው።
👉በዚህም ድርጅቱ የወረቀት ትኬት ሽያጩን ሙሉ ለሙሉ በማስቀረት ወደ ዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ለመሸጋገር ለሚያደርገው ጉዞ መደላድል የሚፈጥር እንደሆነ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews