የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥም ጊዜ መደረግ የሚገባቸዉ የጥንቃቄ እርምጃዎች
ከአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የተሰጠ ማብራሪያ
📌 ከቤት ውጭ ከሆኑ - ከዛፎች፣ ከሕንፃዎች፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።
📌 በቤት ውስጥ ከሆኑ - በበር መቃኖች፣ በኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
📌 በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ- ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
📌 መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ- የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች #በ939 ፈጥነዉ ያሳውቁ- የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን!!
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews