⚽የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ከተማዎች አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ ተገለፀ።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚመራው ይህ ዓመታዊ ውድድር በሁለት ምድቦች ተከፍሎ በ24 ክለቦች መካከል የሚካሄድ ሲሆን ውድድሩ ጥቅምት 17 ጅማሮውን እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል፡፡
በሁለት ምድብ 12 ቡድኖችን የሚይዘው የሊጉ ጨዋታዎች ዘንድሮ ሁለት ክለቦችን ወደ ፕሪሚየር ሊግ የሚያሳልፍ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
በተመሳሳይ በ2016 ዓ.ም የከፍተኛ ሊግ ውድድሩ በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ከተማዎች የተከናወነ ሲሆን በውድድሩ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ከፍ ያደረጋቸውን ውጤት ማስመዝገባቸው የሚታወስ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnew