⚽️ የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በድሬደዋ እስታዲየም ተደርጎ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ምክንያት ለቀናት ተቋርጧል፡፡
በውድድር ዓመቱ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከውድድሩ መሰረዙን ተከትሎ በ18 ተሳታፊ ክለቦች የሚካሄደው ሊጉ ከ4ኛ ሳምንት በኋላ ያለው መርኃ ግብር ማስተካከያ እንደተደረገበት ሊግ ካምፓኒው ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ መሰረት የሊጉ 4ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቅዳሜ ጥቅምት 9 ጀምሮ የሚካሄዱ ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉም ከ5ኛ ሳምንት ውጪ ባሉ የቀሪ ሳምንታት መርኃ ግብሮች ሁለት አራፊ ቡድኖች በየሳምንቱ ይኖራሉ፡፡
የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ድሬዳዋ ከተማ በ6 ነጥቦች እና አራት የግብ ልዩነት እየመራ ሲገኝ ባህርዳር ከተማ እና ሲዳማ ቡና በእኩል ስድስት ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnew
#EBS_SPORTS