የጥቅምት 1/2017 አበይት የአለም ዜናዎች
🇺🇸 የአሜሪካዋን ፍሎሪዳ ግዛት የመታው ሄሪኬን ሚልተን የተሰኘው ከባድ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ ባስከተለው አደጋ በትንሹ 16 ሰዎች ሲሞቱ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንደተቋረጠባቸው ተነገረ።
🇯🇵 የኒውክለር ጦር መሣሪያ አስከፊነት ላይ ቅስቀሳ በማድረግ የሚታወቀው የጃፓኑ የፀረ ኒውክለር ጦር መሣሪያ ድርጅት ኒሆን ሂዳንኪዮ የዘንድሮው የኖቤል ሰላም ሽልማት አሸነፈ።
🇮🇷🇮🇱 የአሜሪካ አጋር የሆኑ የአረብ አገራት ለእስራኤል ትብብር እንዳያደርጉ ኢራን በሚስጥር ማስጠንቀቂያ መስጠቷ ተሰምቷል።
🇺🇸 የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዴሞክራቷ ዕጩ ካምላ ሃሪስ ጋር በቴሌቪዥን በሚካሄድ የቀጥታ ሥርጭት ድጋሚ ክርክር ለማድረግ ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ተናገሩ።
🇱🇧🇮🇱 የሊባኖሱ ጊዜአዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ የእስራኤል ሄዝቦላህ ጦርነት እንዲቆም የሚያደርግ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈረም ጥሪ አቀረቡ።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnew