የተቀናጀ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ እንዲኖር እየተሰራ ነው
የተቀናጀ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ እውን እንዲሆንና በቅንጅት ማነስ ምክንያት የሚደርሰውን የሃብት ብክነት ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ማኔጅመንት ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ገበየሁ ሊካሳ ገልፀዋል፡፡
ተቋሙ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚዘረጋቸውን የመካከለኛና ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች፣ አቅማቸውን ለማሻሻልና ለማዛወር ከመንገዶች ባለስልጣን፣ከኢትዮ-ቴሌኮምና መሰል-ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ መሆኑን ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ተቋማቱ በተናጠል በሚሰሩበት ወቅት አንድ ተቋም የሌላኛውን ተቋም መሰረተ ልማት የማበላሸትና የማጥፋት ሁኔታ ይከሰቱ እንደነበር የገለጹት ዶ/ር ገበየሁ ይህም ለስራ ድግግሞሽና ለኪሳራ ይደረግ እንደነበር አንስተዋል፡፡
በአንፃሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በኮሪደር ልማት የኤሌክትሪክ፣ የውኃ፣ የስልክ፣ የመንገድ ወዘተ መሰረተ-ልማቶች ሲዘረጉ ተቋማት በቅንጅት በመስራታቸው አላስፈላጊ እና ተደጋጋሚ የሆኑ ወጪዎችን እንዲቀንስ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
ተቋሙ የኃይል መቆራረጥን ለማስቀረት በርካታ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች መልሶ ግንባታ እያከናወነ እንደሆነ የጠቀሱት ስራ አስፈፃሚው የተቋማት መቀናጀት ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ፣ደንበኞችም የኃይል አቅርቦት እንዲያገኙ እንዲሁም ግብዓቶች እንዳይጎዱ ማድረግ አስችሏል ብለዋል፡፡
የተጀመሩ የጋራ ስራዎች ለማጠናከርና ቀጣይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ የፌደራል የተቀናጀ መሰረተ-ልማት ማስተባበሪያ ኤጀንሲ አስገዳጅ ደረጃዎችን (ስታንዳርዶችን) አዘጋጅቶ ወደ ስራ ማስገባቱ ይታወሳል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት