የኤሌክትሪክ አደጋን ለመከላከል የሚያግዙ የጥንቃቄ መንገዶች
• በረገቡ የኤሌክትሪክ መስመሮች ስር ሾልኮ ለማለፍ አይሞክሩ፤
• ኃይለኛ ንፋስ በሚነፍስበት ወቅት ከኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ርቀትዎን ጠብቀው ይንቀሳቀሱ፤
• ተበጥሶ የወደቀና የተንጠለጠለ የኤሌክትሪክ ገመድ ወይም ሽቦ ሲያዩ ከመንካት በመቆጠብ ለሚመለከተው አካል ያሳውቁ፤
• በከፍተኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ መስመሮች ስር ወይም አጠገብ ማንኛውንም የግንባታ ሥራ ከማከናወን ይጠበቁ፤
• ህንፃዎች ሲገነቡ ከኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ፤ዛፎች ሲቆረጡ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ እንዳይወድቁ ጥንቃቄ ያድርጉ፤
• የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ከቆርቆሮ ጣሪያ፣ አጥር፣ ከልብስ ማስጫ ገመዶች ጋር እንዳይገናኙ ያድርጉ፤
• የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት በባለሞያ እንዲከናወን ያድርጉ፤
• ደረጃቸውን የጠበቁ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶችን ይጠቀሙ፤
• በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መሳሪያዎች ላይ ቃጠሎ ሲነሳ በውሀ ከማጥፋት በመቆጠብ ትክክለኛውን የእሳት ማጥፊያ ይጠቀሙ፤
• የኤሌክትሪክ መስመሩን ከመቆጣጠሪያው ሳያጠፉ በኤሌክትሪክ የተያዘን ሰው ለማዳን አይሞክሩ፤
• የኤሌክትሪክ ሀይልን ከራስዎ ቆጣሪ ወደ ሌላ ሰው ቤት አሳልፎ ከመዘርጋት ይቆጠቡ፤
• ብረት ነክ የሆኑ ቁሳቁሶችን ከኤሌክትሪክ ሶኬቶች ወይም ማከፋፈያዎች ጋር በፍፁም አያገናኙ፤
• በአንድ ማከፋፈያ ላይ ብዙ ኬብሎችን ማገናኘት ለአደጋ ስለሚያጋልጥ በፍፁም አያድርጉ፤
• በኤሌክትሪክ ሥራ ሲሰሩ ርጥብ ነገሮች ለአደጋ ሊያጋልጥዎ ስለሚችሉ መጠንቀቅ አይዘንጉ፤
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት