ሁለቱ ተቋማት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ለደንበኞች ለማቅረብ ውይይት አደረጉ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ዛሬ ባደረጉት ውይይት አስተማማኝ የሆነ የኃይል አቅርቦት ለደንበኞች ለማድረስ እንደሚሠሩ ገልጿዋል።
በተደረገዉ የጋራ ውይይት የተለያዩ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን በተለይም ከኃይል አቅርቦት ጋር እና ከሃይል መቆራረጥ ጋር በተያያዘ እንዲሁም ለቅድመ መከላከል ጥገናም ሆነ ለማሻሻያና መልሶ ግንባታ ስራ የሚቋረጥ የሃይል መቋረጥ ላይ ሁለቱ ተቋማት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
በውይይቱ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የሃይል ፍላጎት ለማሟላት እና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለደንበኞች ለመስጠት በየደረጃው ያሉ ሃላፊዎች በቅንጅት መሥራትና ከደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን መፍታት እንደሚገባ ተጠቅሷል።
ተቋማቱ እየሠጡት ያለው አገልግሎ ለሃገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሠረት በመሆኑ ያልተቆራረጠና ጥራ ያለው የኃይል አቅርቦት ለመስጠት መደረግ ስለሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
መሠል የምክክር መድረክ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ለማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመላክቷል።
ውይይቱ በሁለቱም ተቋማት ዋና ስራ አስፈጻሚዎችን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ አመራር አባላት መካከል የተካደ ነበር።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት