አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው
በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች ይስተዋሉ የነበሩ የኃይል መቆራረጥን ችግሮችን ለመቀነስ እና አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት በአንድ ትራንስፎርመር ላይ የሚኖርን ከፍተኛ የሃይል ጭነት ማመጣጠን ስራ ተከናውኗል፡፡
የሃይል ማመጣጠን ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ቤላ 1 እና 4፣ ኮተቤ 10፣ ለገጣፎ 11፣ አያት ጂ አይኤስ መስመር 1፣ 2 እና 3፣ ወረገኑ 6 እና 9 እንዲሁም ኮዬ አቦ 4 እና 5 ተጠቃሾች ናቸው፡፡
በነዚህ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የሃይል መቆራረጥ ለመቀነስ የሃይል ማመጣጠን ስራ ከማከናወን ባላፈ በተለያዩ የቅድመ መከላከል ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡
ከተከናወኑ የቅድመ መከላከል ሥራዎች መካከል የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችን ከዛፍ የማፅዳት ስራ አንዱ ሲሆን በዚህም 123.4 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ መስመሮችን ነጻ ማድረግ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ 310 ኪሜ የተጎዱና እና የተበላሹ ምሰሶዎችን መቀየር፣ 28.14 ኪ.ሜ የረገቡ መስመሮችን የማስተካከል እና 319 ኪሜ የተላጡ እና የተሰበሩ ኢንሱሌተሮች የመቀየር ስራ ተከናውኗል፡፡
በተጨማሪ ለቁልፍ ደንበኞች አስተማማኝ እና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ለመስጠት የዲዛይን ስራቸው ከተጀመረ ሲሆን አድዋ ሙዚየም፣ አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽናል ሴንተር እና ግራንድ ፓላስ አካባቢዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
በሌላ በኩል የተወካዮች ምክር ቤት፣ ፍሬንድሺፕ ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚም፣ ብሔራዊ ባንክ፣ የቴሌ ዋና ሳይቶች እንዲሁም ሸራተን እና ሒልተን ሆቴል ዲዛይናቸው ከተጠናቀቁ ደንበኞች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት