የመታር ሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት የመስመር ዝርጋታ 98 በመቶ ደረሰ
በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ዋንተዋ ወረዳ መታር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የመታር ሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት የመስመር ዝርጋታ ሥራ 98 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡
በፕሮጀክቱ 2.1 ኪ.ሜ የመካከለኛ፣ 17 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እና የ4 ትራንስፎርመር ተከላ ስራ የተከናወነ ሲሆን የሶላር ሚኒግሪድ ግንባታ አጠቃላይ ግንባታ 40 በመቶ ደርሷል፡፡
እየተጠናቀቀ የሚገኘው የመስመር ዝርጋታ 20 ሚሊየን ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን ለኃይል ማመነጫ ግንባታው ደግሞ 532 ሺህ 682.74 ዶላር እና 7 ሚሊየን 231 ሺህ 714 ብር በጀት ተይዞለታል፡፡
የፕሮጀክቱ ግንባታ እየተከናወነ የሚገኘው ሲ.ኢ.ቲ እና ኤን.አር በተባሉ ሁለት የቻይና ኮንትራክተሮች አማካኝነት ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ እስከ 250 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጭ ይሆናል፡፡
የፀሐይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱን ቀሪ ሥራዎች በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በአካባቢው የሚገኙ የጤና ተቋማት፣ የእርሻ ማዕከላት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ የውሃ ተቋማትና ሌሎችም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት