ከ21 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአገር አቀፍ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም 21 ሺህ 104 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድርግ ችሏል፡፡
በፕሮግራሙ በተጠናቀቀው የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ተጠቃሚ ከሆኑ አዳዲስ ደንበኞች ውስጥ 6 ሺህ 455 በኦሮሚያ ፣ 6 ሺህ 306 በአማራ፣ 2 ሺህ 374 በትግራይ፣ 288 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ 64 በጋምቤላ ክልል እና ሌሎች ደግሞ በሌሎች ክልሎች የሚገኙ ናቸው፡፡
ደንበኞችን ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ 639 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣1 ሺህ 61 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እና 245 ትራንስፎርመር ተከላ ስራ ተከናውኗል፡፡
በተመሳሳይ በዋናው የኃይል ቋት እና በፀሐይ ኃይል ምንጭ የገጠር ከተሞችን በማገናኘት አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
ተቋሙ ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው በገጠሩ የሃገራችን ክፍል የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን አማራጭ የሃይል ምንጮችን በመጠቀም ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት