ሪጅኑ 15ሺ 3መቶ 28 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ አደረገ
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባህርዳር ሪጅን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 15ሺ 3መቶ 28 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ በማድረግ የዕቅዱን 76 በመቶ አሳክቷል፡፡
አዳዲስ ደንበኞችን ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ 63 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣134 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታና 175 ትራንስፎርመር የማስቀመጥ ስራ ማከናወን ችሏል፡፡
በዚህም ከመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ደንበኞች በተጨማሪ የትምህርት፣የውሃ ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡
በሪጅኑ ባለፋት 9 ወራት በተሰራ የመልሶ ግንባታ ስራ 194 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣ 123 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እንዲሁ 41 የተለያየ አቅም ያላቸው የትራንስፎርመር ተከላ ስራ አከናውኗል። በዚህም የኃይል መቆራረጥ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች መቅረፍ ተችሏል።
እንደተቋም በተያዘው የኃይል መቆራረጥ ችግር የመቀነስ ዕቅድ ለማሳካት 3ሺህ 982 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር 1641 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ቅድመ ጥገና ስራ ማከናወን ችሏል፡፡
በቅድመ ጥገና ስራው ያዘመሙ ምሰሶዎች የመቀየር ስራ፣ በኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮች ላይ የገቡ ዛፎችን ማፅዳት፣ የተሰባበሩ ስኒዎችን የመቀየር ስራ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ሪጅኑ ለ228 ሺህ 126 ደንበኞች አገልግሎት እየሠጠ ሲሆን 29 የደንበኞች ማዕከላት እና 417 የሳተላይት ጣቢያዎች አሉት፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት