ከሰሞኑ አንድ፣ ሁለት ወይም ሶስት የሚሆኑ በመንግስት የተሰሩ ስራዎች ትክክል መስለው ስለታዩኝ 'መልካም ነው' ብዬ ከመፃፌ አንዳንዶች 'ምን ነክቶህ ነው?' እና 'ተቀላቀልካቸው እንዴ?' የሚል መልእክት አድርሰውኛል 😊
ድሮም ሆነ አሁን አስተያየት፣ ጥቆማ እና ትችት የማቀርበው ሊጠቅም ከቻለ በሚል ነው... ጥቅም ሲሰጥም ስላየሁበት። የማቀርባቸው መረጃዎች ደግሞ ለሀገር እንደ አንድ የሚድያ ባለሙያ ግዴታ ከመወጣት እና ለህዝብ ድምፅ ከመሆን አንፃር ነው።
ከዛ ውጪ በትግራይ ይደርስ የነበረውን ግፍ ስፅፍ 'ጁንታ' የተባልኩት ግለሰብ ዛሬም በአማራ ክልል የሚደርሰውን ሰቆቃ ለህዝብ ሳቀርብ 'ጃዊሳ' እየተባልኩ ነው፣ አንድ ሰሞን በኦሮሚያ ሰላማዊ ዜጎች ተገደሉ የሚል ዜና ሰርቼ 'ሸኔ' የሚል ስም ተሰጥቶኝም ነበር። ስም ልጠፋው ስለለመድኩት እና ስለማይደንቀኝ አጠናክሮ መቀጠል ይቻላል።
ነገር ግን እኔ እዛው የድሮ አቋሜ ላይ እገኛለሁ፣ የማንም ደጋፊ ወይም ተቃዋሚ አይደለሁም። ያለሁበት ይህ ቦታ ስለተመቸኝ ወደፊትም መገኛዬ እዛው ነው 📍
መልካም ምሽት።
@EliasMeseret