#FakeNewsAlert ይህ መረጃ ነጭ ውሸት ነው!
ቀላሉ ማስረጃ እና ማንም በሰከንዶች ጉግል አድርጎ የሚረዳው ሀቅ አለ፣ እሱም እሷ በለጠፈችው ፎቶ ላይ የሚታየው እና ታድሶ መብረር ቻለ ተብሎ በመንግስት ሚድያዎች ጭምር ስሙ ተጠቅሶ የነበረው DHC Buffalo የተባለ የካናዳ ስሪት አውሮፕላን ሲሆን እሷ የምታወራው ስለ ሶቪየት ህብረት ስሪት አውሮፕላን ነው። ማስረጃው: https://www.baesystems.com/en/heritage/de-havilland-canada-dhc-5-buffalo
ምናልባት ለማለት የፈለገችው በአንድ ወቅት ሶቪየቶች ለኮ/ል መንግስቱ ሰጥተውት ስለነበረው "መሸሻ" የሚል ቅፅል ስም ስለነበረው አውሮፕላን ሊሆን ይችላል፣ እሱ ግን ሌላ አውሮፕላን ነው።
ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል እና፣ ስለዚህ "መሸሻ" ስለተባለ የሶቪየት አውሮፕላን በቅርቡ የሰማሁትን ላካፍላችሁ።
ሶቪየቶች ይህን አውሮፕላን ለኮ/ል መንግስቱ ከሰጡ በኋላ ፕሬዝደንቱ አልተጠቀሙበትም ነበር። ሙሉ ነጭ የተቀባው እና ጭራው ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ ያለው "መሸሻ" ለበርካታ አመታት በቢሾፍቱ አየር ሀይል ግቢ ቆሞ ነዋሪዎች ያዩት ነበር።
ከዛም ኢህአዴግ ከገባ በኋላ እና ሜቴክ ከተቋቋመ በኋላ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ይህን የሶቪየት አውሮፕላን ለጠ/ሚር መለስ ዜናዊ የ VIP አውሮፕላን እንዲሆን እቀይረዋለሁ በማለት ቆራርጠው፣ ቀጥለው፣ ነቃቅለው፣ ሰካክተው ጨረሱ።
ከዛ ለበረራ ብቁነት ምዝገባ ሲቪል አቪዬሽንን ሲጠይቁ ተቆጣጣሪዎቹ "ይሄ ለበረራ ብቁ አይደለም" ብለው ፍቃድ እንደተከለክሉ እና ከዛ በኋላም ቆሞ እንደቀረ ሰምቻለሁ።
* ከላይ ያለውን መረጃ የፃፍሽው ትክክለኛው የኮ/ል መንግስቱን ትዝታዎችን የፃፍሽው ትግስት አየለ ከሆንሽ መንግስቱ የነገሩሽን ደግመሽ አጣሪ፣ ይሄ የካናዳ ስሪት አውሮፕላን እንጂ የሶቪየት አውሮፕላን አይደለም።
@EliasMeseret