ተወለደ በበረት
"እነሆ ታላቅ የምስራች እነግራችኋለሁ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት ኢየሱስ ተወልዷልና ታገኙታለችሁ ቤተልሔም በታላቅ ትህትና ታገኙታለችሁ በግርግም በታላቅ ትህትና"
ተወለደ በበረት የአለም መድኃኒት
'ኢየሱስ አልፋ ኦሜጋ መጥቷል እኛን ፍለጋ/2/
የአለማትን ጠቅላይ ጨርቅ ጠቀለለው
የክብርን ባለቤት ፍጥረት አቃለለው
የሁሉ ማደርያ ቤተልሔም ሲያድር
በአንድነት ዘመሩ ሰማይና ምድር ይሁንለት ብለው
አዝ_
አዳምን ሊታደግ ከገሃነም ቁጣ
በተዘጋው ደጃፍ ልዑል ገብቶ ወጣ
ከማርያም ተወልዶ በኅቱም ድንግልና
ትህትናን አብዝቶ አጨን ለልዕልና ለስሙ ምስጋና
አዝ_
በአምሳላችን መጥቶ በአምሳሉ ወለደን
በበረት ተወልዶ አርያም ወሰደን
ለክብር አበቃን በበዛ ውርደቱ
እንደገና ልደት ሆነልን ልደቱ ታደገን መምጣቱ
አዝ_
ከሰማያት ወርዶ እንዲያሰፍን ሰላም
በበረት ውስጥ ሞቀ እስትንፋስን ከላም
ህጻን ተወለደ ወንድ ልጅ ተሰጠን
አጨን ለከፍታ በትህትናው መጠን ከሞት አስመለጠን
አዝ_
የነፍስን እረኛ ጎበኙት እረኞች
የጥበብን አባት አዩት ጥበበኞች
ስጦታ ተሰጠው የአለም ስጦታ
ልደት ታሰበለት የልደታት ጌታ ሁሉን ሞላው ደስታ
አዝ_
አዳምን ሊታደግ ከገሃነም ቁጣ
በተዘጋው ደጃፍ ልዑል ገብቶ ወጣ
ከማርያም ተወልዶ በኅቱም ድንግልና
ትህትናን አብዝቶ አጨን ለልዕልና ለስሙ ምስጋና
ዘማሪ ሊቀ ዲያቆናት ነብዩ ሳሙኤል
✟እንዘምር✟
እን_ዘም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እን_ዘ_ም__ር
"እነሆ ታላቅ የምስራች እነግራችኋለሁ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት ኢየሱስ ተወልዷልና ታገኙታለችሁ ቤተልሔም በታላቅ ትህትና ታገኙታለችሁ በግርግም በታላቅ ትህትና"
ተወለደ በበረት የአለም መድኃኒት
'ኢየሱስ አልፋ ኦሜጋ መጥቷል እኛን ፍለጋ/2/
የአለማትን ጠቅላይ ጨርቅ ጠቀለለው
የክብርን ባለቤት ፍጥረት አቃለለው
የሁሉ ማደርያ ቤተልሔም ሲያድር
በአንድነት ዘመሩ ሰማይና ምድር ይሁንለት ብለው
አዝ_
አዳምን ሊታደግ ከገሃነም ቁጣ
በተዘጋው ደጃፍ ልዑል ገብቶ ወጣ
ከማርያም ተወልዶ በኅቱም ድንግልና
ትህትናን አብዝቶ አጨን ለልዕልና ለስሙ ምስጋና
አዝ_
በአምሳላችን መጥቶ በአምሳሉ ወለደን
በበረት ተወልዶ አርያም ወሰደን
ለክብር አበቃን በበዛ ውርደቱ
እንደገና ልደት ሆነልን ልደቱ ታደገን መምጣቱ
አዝ_
ከሰማያት ወርዶ እንዲያሰፍን ሰላም
በበረት ውስጥ ሞቀ እስትንፋስን ከላም
ህጻን ተወለደ ወንድ ልጅ ተሰጠን
አጨን ለከፍታ በትህትናው መጠን ከሞት አስመለጠን
አዝ_
የነፍስን እረኛ ጎበኙት እረኞች
የጥበብን አባት አዩት ጥበበኞች
ስጦታ ተሰጠው የአለም ስጦታ
ልደት ታሰበለት የልደታት ጌታ ሁሉን ሞላው ደስታ
አዝ_
አዳምን ሊታደግ ከገሃነም ቁጣ
በተዘጋው ደጃፍ ልዑል ገብቶ ወጣ
ከማርያም ተወልዶ በኅቱም ድንግልና
ትህትናን አብዝቶ አጨን ለልዕልና ለስሙ ምስጋና
ዘማሪ ሊቀ ዲያቆናት ነብዩ ሳሙኤል
✟እንዘምር✟
እን_ዘም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እን_ዘ_ም__ር