ምኩራብ፡ የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት
መ/ር ጌታቸው በቀለ
የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት “ምኩራብ” በማለት ይጠራል ጌታችን አምላካችን መድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ምኩራብ የገባበትና ያስተማረበት ነው፡፡
በሰንበታቱ ውስጥ የሚነበበውና የሚዘመረውም ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ያስተማራቸውን ትምህርቶችና የሠራቸውን ዋና ዋና ተዓምራትና መንክራት የሚመለከቱ ናቸው፡፡ ጾሙ የጌታ ጾም ስለሆነ ሁሉም መዝሙራትና ምንባባት ከጌታ ትምህርትና ሥራ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ በዚህ መሠረት ሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ ተሰይሟል፡፡“ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ” እንዲል፤ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያነ ሥጋን በትምህርቱ፣ ድውያነ ነፍስን በተአምራቱ ሲፈውስ በምኩራብ እየተገኘ የፈጸመውን የማዳን ሥራ በኀሊና እያሳሰበ የሚያስተምር ሦስተኛ ሳምንት ነው /ዮሐ. ፪፥፲፪/፡፡
በዚህ ሳምንት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መሄዱን፣ በቤተመቅደሱ የማይገባ ንግድ ያደርጉ የነበሩትን “የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ” ብሎ መገሰፁን፣ የሚሸጡ የሚለውጡትንም መገለባበጡን፣ ደቀ መዛሙርቱም ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት አስቀድሞ በትንቢት “የቤትህ ቅናት በላኝ” በማለት የተናገረው እንደተፈጸመ ማስተዋላቸው የሚታሰብበትና የሚተነተንበት ነው /ዮሐ. ፪ ፥፲፫-፲፯/፡፡
ምኩራብ በዘመነ ብሉይ
በብሉይ ኪዳን ዘመን በኢሩሳሌም የአይሁድ ቤተመቅደስ ነበራቸው፡፡ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተመቅደሱን አፈረሰ ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሠሩ ነበር፡፡ በምኩራብ ውስጥም የሕግ መጽሐፍትና በነቢያት የተጻፉ ጽሑፎች በብራና ጥቅልል ይገኛሉ፡፡ ምዕመኑ እንዲሰማቸው እንደ መድረክ ባለ ቦታ ላይ ካህናትና መምህራን ቆመው መጽሐፍትን ያነባሉ ቃለ እግዚአብሔርንም ያስተምሩ ነበር። ምኩራብን የሚመሩት አለቆች ጥፋተኛ ሰው ሲገኝ በመግረፍ ወይም ከምኩራብ በማስወጣት ሊቀጡ ሥልጣን ነበራቸው፡፡ አገልጋይ ወይም የሚራዱ ወጣቶችም ልጆችን በማስተማር ጥቅሎችን በማቅረብ በተጨማሪ የአለቆችን ትዕዛዝ በመፈጸም ያገለግላሉ፡፡በየሰንበቱ ሕዝብ ሁሉ በምኩራብ ተሰብስበው አምልኮታቸውን ይፈጸሙ ነበር፡፡ ከአምልኮታቸው ውስጥ ጸሎት፤ ከሕግና ከነቢያት ንባብ ፤ ስብከትና ቡራኬ ነበር፡፡
ጌታችን በምኩራብ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱና በቃና ዘገሊላ ተዓምራቱ አምላክነቱን ገልጦ ሕዝቡን ማስተማር ከመጀመሩ በፊት በነበሩት ሠላሳ ዓመታት በተደጋጋሚ ወደ ቤተመቅደስ መጥቷል፡፡ ከእነዚህም መካከል በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉት በሥርዐተ ኦሪት መሠረት በተወለደ በዐርባኛው ቀን ወደ ቤተ መቅደስ መምጣቱ /ሉቃ. ፪፥፳፪-፵/፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ ከዮሴፍና ከእመቤታችን ጋር ለበዓል ወደ ኢየሩሳሌም በሄዱ ጊዜ ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ቤተመቅደስ በመሄድ የኦሪት ሊቃውንትን ሲጠይቃቸውና ሲሰማቸው የነበረ መሆኑ ናቸው /ሉቃ.፪፥፵፩-፵፯/፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጣ አገልጋዮቹ በሥጋዊ ፍላጎታቸው ምክንያት በቤተመቅደሱ የማይገባ ሥራ እየሰሩ ቢያይም አምላክነቱን ገልጦ የሚያስተምርበት፣ የሚገስጽበት ጊዜ አልደረሰምና በዝምታ አልፏቸው ነበር፡፡
ጊዜው በደረሰ ጊዜ ሊቃናተ አይሁድ ባለመታዘዝ ያረከሱትን መቅደሱን ያነጻ ዘንድ መጣ፡፡ መሥዋዕተ ኦሪት ይሠዋበት የነበረውን ቤተመቅደስ ያነፃው ጌታ ራሱን የሐዲስ ኪዳን መስዋእት አድርጎ አቅርቧልና ኃላፊ ጠፊ የሆኑትን የብሉይ ኪዳን የመስዋእት እንስሳት ከቤተ መቅደስ አስወጣ፡፡