ስንት ፍጡር አለ?
~~~
አባቱ ላይ የሚጀነን … እናቱ ላይ ’ሚደነፋ
ወላጆቹ የሚፈሩት … ስነ ምግባሩ የከረፋ
ስንት ከንቱ ፍጡር አለ … አኺራውን እሚያጠፋ?
ጉርምስናውን ተጠቅሞ ወላጆቹን የሚገፋ
ሳይሞቅ ፈላ የጥጃ ቀንዳም ሽቅብ ምራቁን የሚተፋ
|
አራስ ነብር ሆኖ ገብቶ … ሳር ቅጠሉን የሚያስጨንቅ
ከባእድ ጋ እየተላፋ … ሚስቱን ልጁን የሚያሳቅቅ
ስንት ብኩን ፍጡር አለ … አስተሳሰቡ የተዘጋ
ለቤተሰብ የማይመች … የውጭ አልጋ የቤት ቀጋ
|
ምላሷ እንደ ጦር የሚዋጋ … እንደ ብጉንጅ የምትነዘንዝ
ለባሏ ጀርባ ሰጥታ … ከባእድ ጋር የምትላዘዝ
ስትወጣ ጥርሷ 64 … ምላሷ ማር የሚተፋ
ከቤቷ የእሳት ወላፈን … ሁለ ነገሯ የጠፋ
ስንት ከንቱ ፍጡር አለች …
ኢስላም፣ ሞራል የማይገዳት
በራሷ ዛቢያ የምትዞር … መላ ቅጡ የጠፋባት?
📲 አድራሻችን ፦
𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥👉🏿@tewihd
Add ያድርጉ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~
𝐠𝐫up👉🏿@tewhiddd
~~~
አባቱ ላይ የሚጀነን … እናቱ ላይ ’ሚደነፋ
ወላጆቹ የሚፈሩት … ስነ ምግባሩ የከረፋ
ስንት ከንቱ ፍጡር አለ … አኺራውን እሚያጠፋ?
ጉርምስናውን ተጠቅሞ ወላጆቹን የሚገፋ
ሳይሞቅ ፈላ የጥጃ ቀንዳም ሽቅብ ምራቁን የሚተፋ
|
አራስ ነብር ሆኖ ገብቶ … ሳር ቅጠሉን የሚያስጨንቅ
ከባእድ ጋ እየተላፋ … ሚስቱን ልጁን የሚያሳቅቅ
ስንት ብኩን ፍጡር አለ … አስተሳሰቡ የተዘጋ
ለቤተሰብ የማይመች … የውጭ አልጋ የቤት ቀጋ
|
ምላሷ እንደ ጦር የሚዋጋ … እንደ ብጉንጅ የምትነዘንዝ
ለባሏ ጀርባ ሰጥታ … ከባእድ ጋር የምትላዘዝ
ስትወጣ ጥርሷ 64 … ምላሷ ማር የሚተፋ
ከቤቷ የእሳት ወላፈን … ሁለ ነገሯ የጠፋ
ስንት ከንቱ ፍጡር አለች …
ኢስላም፣ ሞራል የማይገዳት
በራሷ ዛቢያ የምትዞር … መላ ቅጡ የጠፋባት?
📲 አድራሻችን ፦
𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥👉🏿@tewihd
Add ያድርጉ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~
𝐠𝐫up👉🏿@tewhiddd