"እኔ ቃል ተመልቻለሁና በውስጤም ያለ መንፈስ አስገድዶኛልና በተሃ ጠጅ እንደተሞላና ሊቀደድ እንደቀረበ አቁማዳ ሊፈነዳ እንደማይችል እንደ ወይን ጠጅ አቁማዳ እነሆ አንጀቴ ሆነ ጥቂት እንድተነፍሰ እናገራለሁ ከንፈሬን ገልጨ እመልሳለሁ
መጽሐፈ ኢዮብ 32፡ 18–20
ከላይ በእግዚአብሔር ቃል እንደተመለከተው ይህንን መልእክት እናገር ዘንድ ግድ ስለሆነብኝ እናገራለሁ፡
ላለመናገር ላለመተንፈስ ከራሴም ከፈጣሪየም ጋር ተሟግቻለሁ፡፡ እንደ ዮናስም እምቢ ብያለሁ፡፡ ይሁንና ከእግዚአብሔር ኃይል ጋር ተሟግቼ ስላልቻልኩ፣ እየከፋኝ ይህንን ትእዛዝ እፈጽም ዘንድ ግድ ሆነብኝ፤ ስለዚህም እንሆ እናገረው ዘንድ የሚገባኝን የዓላማችንን መጻኢ ሁኔታ እናገራለሁ፡፡"
🗞 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት 1 ገጽ 1፤ ተጻፈ ኅዳር 7/1998 ዓ.ም
🟢🟡🔴 ተወዳጆች የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦቻችን የአጋዕዝተዓለም ሥላሴና የቅድስት ድንግል ማርያም መልዕክት ለሆነው እንኳን ለታላቁ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የመጀመሪያ (1ኛ) መልዕክት የተጻፈበትና ለመላው የአዳም ዘር የተላለፈበት 19ኛ ዓመት አደረሳችሁ አደረሰን!
🇨🇬 "በድቅድቅ ጨለማ (በቀቢጸ ተስፋ) ላሉት ብርሃን በራላቸው" እንዳለ መጽሐፍ እውነተኛ ኢትዮጵያዊያን የተዋሕዶ ልጆች ተስፋ ቆርጠን በጠፋንበት ዘመን እግዚአብሔር ድምጹን ያሰማን፣ ፈቃዱን ያሳወቀን በመጀመሪያይቱ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት የዛሬ 19 ዓመት በኅዳር 7 ቀን 1998 ዓ.ም እንደዚህች ባለችቱ ቀን ነበር። ይኸው ለእኛ ለኢ/ዓ/ብ ቤተሰቦች 19 ወርቃማ ዘመናት በእሳት መፈተኛ ሆነውን በንቅለ ተከላ ውስጥ እያለፍን እንገኛለን። አሁንም ቀሪውን አሳልፎ ሕግጋተ ሥላሴ ፀንቶ ኢትዮጵያ ለዓለም ገዢና ብርሃን ለምትሆንበት የትንሣኤው ዘመን ያድርሰን!! አሜን!
🔊 ኅዳር 7/2017 ዓ.ም