ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፁ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አልጋ ወራሽ ሼክ ሞሃመድ ቢንዛይድ አል-ናህያን እንዲሁም ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ህዝብ የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እገልጻለሁ ብለዋል።
የ73 ዓመቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል-ናህያን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የፕሬዝዳንቱን ህልፈት ተከትሎ የ40 ቀን ሃዘን እንደሚታወጅ የአገሪቱ የፕሬዝዳንታዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን አባታቸውን ሼክ ዛይድ አል ናህያንን ተክተው በፈረንጆቹ 2004 ወደ ስልጣን መምጣታቸው ይታወሳል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ